La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ሳሙኤል 9:27 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ወደ ከተማዪቱ ዳርቻ እየወረዱ ሳለ፣ ሳሙኤል ሳኦልን፣ “አገልጋይህ ወደ ፊት ቀድሞን እንዲሄድ ንገረው” አለው፤ አገልጋዩም እንደ ተነገረው አደረገ፤ ከዚህ በኋላ ሳሙኤል፣ “አንተ ግን ከእግዚአብሔር የተላከ መልእክት እነግርህ ዘንድ ለጥቂት ጊዜ እዚህ ቈይ” አለው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ወደ ከተማዪቱ ዳርቻ እየወረዱ ሳለ፥ ሳሙኤል ሳኦልን፥ “አገልጋይህ ወደ ፊት ቀድሞን እንዲሄድ ንገረው፤ አገልጋይህም እንዳለፈ፥ አንተ ግን ከጌታ የተላከ መልእክት እንድነግርህ ለጥቂት ጊዜ እዚህ ቆይ” አለው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ወደ ከተማይቱም ዳርቻ በደረሱ ጊዜ ሳሙኤል ሳኦልን “አገልጋይህ ቀድሞን ወደ ፊት እንዲሄድ ንገረው” አለው፤ አገልጋዩም ቀድሞ ከሄደ በኋላ ሳሙኤል ሳኦልን እንደገና “አንተ እዚህ ትንሽ ቈይ፤ እኔም እግዚአብሔር ያለውን ሁሉ እነግርሃለሁ” አለው።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እነ​ር​ሱም በከ​ተ​ማ​ዪቱ ዳር ሲወ​ርዱ ሳሙ​ኤል ሳኦ​ልን፥ “ብላ​ቴ​ናው ወደ ፊታ​ችን እን​ዲ​ያ​ልፍ እዘ​ዘው፤ አንተ ግን ከእኔ ጋር ከዚህ ቁምና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስማ” አለው። ብላ​ቴ​ና​ውም አለፈ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እነርሱም በከተማይቱ ዳር ሲወርዱ ሳሙኤል ሳኦልን፦ ብላቴናውን ወደ ፊታችን እንዲያልፍ እዘዘው፥ አንተ ግን የእግዚአብሔርን ቃል አሰማህ ዘንድ በዚህ ቁም አለው። ብላቴናውም አለፈ።

Ver Capítulo



1 ሳሙኤል 9:27
7 Referencias Cruzadas  

ከዚያም ኢሳይያስ ሕዝቅያስን እንዲህ አለው፤ “የእግዚአብሔርን ቃል ስማ፤


ከዚያም ሳሙኤል የዘይቱን ብርሌ ወስዶ፣ ዘይቱን በሳኦል ራስ ላይ ካፈሰሰ በኋላ እንዲህ ሲል ሳመው፤ “በርስቱ ላይ ገዥ ትሆን ዘንድ እግዚአብሔር ቀብቶህ የለምን?


ሳሙኤልም ሳኦልን፣ “ስማ! ትናንት ማታ እግዚአብሔር የነገረኝን ልንገርህ?” አለው። ሳኦልም፣ “ንገረኝ” ሲል መለሰለት።


በማለዳ ተነሡ፤ ሳሙኤል ሳኦልን ከሰገነቱ ላይ ጠርቶ፣ “ላሰናብትህ ስለ ሆነ ተዘጋጅ” አለው። ሳኦልም ተዘጋጅቶ እንዳበቃ፣ ከሳሙኤል ጋራ ተያይዘው ወደ ውጭ ወጡ።