La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ሳሙኤል 9:24 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ወጥ ቤቱም የጭኑን ሥጋ እንዳለ አምጥቶ በሳኦል ፊት አስቀመጠው። ሳሙኤልም፣ “ይህ፣ ‘እንግዶችን ጋብዣለሁ’ ካልሁበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ተወሰነው ጊዜ ድረስ ለአንተ ተለይቶ የተቀመጠልህ ስለ ሆነ ብላው” አለው። ሳኦልም በዚያች ዕለት ከሳሙኤል ጋራ ዐብሮ በላ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ወጥ ቤቱም የጭኑን ሥጋ እንዳለ አምጥቶ በሳኦል ፊት አስቀመጠው። ሳሙኤልም፥ “ይህ፥ እንግዶችን ጋብዣለሁ ካልሁበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ተወሰነው ጊዜ ድረስ፥ ለአንተ ተለይቶ የተቀመጠልህ ስለሆነ ብላው” አለው። ሳኦልም በዚያች ዕለት ከሳሙኤል ጋር አብሮ በላ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ስለዚህም የወጥቤቱ ሠራተኛ ምርጥ የሆነውን የታናሽ ብልት ሥጋ አምጥቶ በሳኦል ፊት አስቀመጠ፤ ሳሙኤልም ሳኦልን “ተመልከት፤ ይህ ለአንተ ተለይቶ የተቀመጠልህ ምርጥ ሥጋ ነው፤ እኔ ከጋበዝኳቸው እንግዶች ጋር ሆነህ እንድትበላ ያስቀመጡልህ ስለ ሆነ እርሱን ተመገብ” አለው። ስለዚህም በዚያ ቀን ሳኦል ከሳሙኤል ጋር አብሮ ተመገበ፤

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ወጥ​ቤ​ቱም ወር​ቹን አም​ጥቶ በሳ​ኦል ፊት አኖ​ረው። ሳሙ​ኤ​ልም፥ “ሳኦ​ልን ለም​ስ​ክር ከባ​ል​ን​ጀ​ራህ ተለ​ይቶ ቀር​ቦ​ል​ሃ​ልና እነሆ፥ በል​ተህ የተ​ረ​ፈ​ህን በፊ​ትህ አኑር” አለው። በዚ​ያም ቀን ሳኦል ከሳ​ሙ​ኤል ጋር በላ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ወጥቤቱም ጭኑንና በእርሱ ላይ የነበረውን አምጥቶ በሳኦል ፊት አኖረው። ሳሙኤልም፦ ሕዝቡን ከጠራሁ ጀምሮ እስከ ተወሰነው ጊዜ ድረስ ለአንተ ተጠብቆአልና እነሆ፥ የተቀመጠልህን በፊትህ አኑረህ ብላው አለ። በዚያም ቀን ሳኦል ከሳሙኤል ጋር በላ።

Ver Capítulo



1 ሳሙኤል 9:24
6 Referencias Cruzadas  

“ከዚህ አውራ በግ ሥቡን፣ ላቱን፣ በሆድ ዕቃው ውስጥ ያለውን ስብ፣ የጕበቱን ሽፋን፣ ሁለቱን ኵላሊቶችና በዙሪያቸው ያለውን ሥብና ቀኙን ወርች ውሰድ፤ ይህ የክህነት አውራ በግ ነው።


“ለአሮንና ለወንዶች ልጆቹ ለክህነት የሆኑትን የአውራውን በግ ብልቶች ቀድሳቸው። የተወዘወዘውን ፍርምባና የቀረበውን ወርች


ሙዳ፣ ሙዳ ሥጋ፣ ምርጥ ምርጡን ቍርጥ ሁሉ፣ ጭንና ወርቹን ጨምርበት፤ የተመረጡ ዐጥንቶችንም ሙላበት።


የሚወዘወዘው ቍርባን ፍርምባና የቀኙ ወርች የአንተ እንደ ሆነ ሁሉ የእነዚህም ሥጋ የአንተ ይሆናል።


ሳሙኤልም ወጥ ቤቱን፣ “ለይተህ አስቀምጥ ብዬ የሰጠሁህን የሥጋ ብልት አምጣው” አለው።