1 ሳሙኤል 9:11 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በከተማዪቱ መዳረሻ ያለውን ኰረብታ በመውጣት ላይ ሳሉ፣ ውሃ ለመቅዳት የሚወጡ ልጃገረዶችን አግኝተው፣ “ባለራእዩ እዚህ ነውን?” ሲሉ ጠየቁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በከተማዪቱ መዳረሻ ያለውን ኰረብታ በመውጣት ላይ ሳሉ፥ ውሃ ለመቅዳት የሚወጡ ልጃገረዶችን አግኝተው፥ “ባለ ራእዩ እዚህ አለን?” ሲሉ ጠየቋቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዳገቱ አድርገው ወደ ከተማው ሲወጡ ውሃ ለመቅዳት የሚወጡ ልጃገረዶችን አግኝተው “ባለ ራእይ እዚህ አለን?” ብለው ጠየቁአቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በከተማዪቱም ዳገት በወጡ ጊዜ ቈነጃጅት ውኃ ሊቀዱ ሲወጡ አገኙና፥ “ባለ ራእይ በዚህ አለ ወይ?” አሉአቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በከተማይቱም ዳገት በወጡ ጊዜ ቆነጃጅት ውኃውን ሊቀዱ ሲወጡ አገኙና፦ ባለ ራእይ በዚህ አለ ወይ? አሉአቸው። |
እርሱም ገና ጸሎቱን ሳይጨርስ፣ እነሆ፤ ከአብርሃም ወንድም ከናኮርና ከሚስቱ ከሚልካ የተወለደው የባቱኤል ልጅ ርብቃ እንስራዋን በትከሻዋ ላይ አድርጋ ብቅ አለች።
የዝማሬ ድምፅ ስሙ። ይህም የእግዚአብሔር የጽድቅ ሥራ፣ ጦረኞቹም በእስራኤል ያደረጉትን ያስታውሳል። “ከዚያም የእግዚአብሔር ሕዝቦች፣ ወደ ከተማዪቱ በሮች ወረዱ።