ስለዚህ የተሰጣቸውን ወይፈን ወስደው አዘጋጁት። ከዚያም ከጧት እስከ እኩለ ቀን የበኣልን ስም ጠሩ፤ “በኣል ሆይ ስማን” እያሉ ጮኹ፤ ድምፅ ግን የለም፤ የሚመልስ አልነበረም፤ በሠሩት መሠዊያ ዙሪያም እየዘለሉ ያሸበሽቡ ነበር።
1 ሳሙኤል 5:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የአሽዶድም ሰዎች በማግስቱም ማለዳ ተነሥተው ሲመለከቱ እነሆ፣ ዳጎን በእግዚአብሔር ታቦት ፊት መሬት ላይ በግንባሩ ተደፍቶ አገኙት። ከዚያም አንሥተው ወደ ቦታው መለሱት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የአሽዶድም ሰዎች በማግስቱ ማለዳ ተነሥተው ሲመለከቱ እነሆ፥ ዳጎን በጌታ ታቦት ፊት መሬት ላይ በግንባሩ ተደፍቶ አገኙት። ከዚያም አንሥተው ዳጎንን ወደ ቦታው መለሱት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በማግስቱም ማለዳ የአሽዶድ ሰዎች ተነሥተው ሲመለከቱ የዳጎን ምስል ሐውልት በእግዚአብሔር የቃል ኪዳን ታቦት ፊት በግንባሩ መሬት ላይ ተደፍቶ አዩት፤ ከዚያም አንሥተው ቀድሞ በነበረበት ስፍራ አቆሙት፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በነጋውም የአዛጦን ሰዎች ማለዱ፤ ወደ ዳጎንም ቤት ገቡ፤ እነሆም፥ ዳጎን በእግዚአብሔር ታቦት ፊት በምድር ላይ በግንባሩ ወድቆ አገኙት፤ ዳጎንንም አንሥተው በስፍራው አቆሙት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በነጋውም የአዛጦን ሰዎች ማለዱ፥ እነሆም፥ ዳጎን በእግዚአብሔር ታቦት ፊት በምድር ላይ በግምባሩ ወድቆ ነበር፥ ዳጎንንም አንሥተው ወደ ስፍራው መለሱት። |
ስለዚህ የተሰጣቸውን ወይፈን ወስደው አዘጋጁት። ከዚያም ከጧት እስከ እኩለ ቀን የበኣልን ስም ጠሩ፤ “በኣል ሆይ ስማን” እያሉ ጮኹ፤ ድምፅ ግን የለም፤ የሚመልስ አልነበረም፤ በሠሩት መሠዊያ ዙሪያም እየዘለሉ ያሸበሽቡ ነበር።
“እኔም በዚያች ሌሊት በግብጽ ምድር ላይ ዐልፋለሁ፤ ከሰውም ከእንስሳም የተወለደውን የበኵር ልጅ ሁሉ እገድላለሁ፤ የግብጽን አማልክት ሁሉ እፈርድባቸዋለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።
ስለ ግብጽ የተነገረ ንግር፤ እነሆ፤ እግዚአብሔር በፈጣን ደመና ላይ ተቀምጦ ወደ ግብጽ ይመጣል፤ የግብጽ ጣዖቶች በፊቱ ይርዳሉ፤ የግብጻውያንም ልብ በውስጣቸው ይቀልጣል።
እንዲህ ያለውን መባ ማቅረብ የማይችል ምስኪን ድኻ፣ የማይነቅዝ ዕንጨት ይመርጣል፤ የማይወድቅ ምስልን ለማቆምም፣ ታዋቂ የእጅ ጥበብ ባለሙያ ይፈልጋል።
የእጅ ጥበብ ባለሙያው የወርቅ አንጥረኛውን ያበረታታዋል፤ በመዶሻ የሚያሳሳውም፣ በመስፍ ላይ የሚቀጠቅጠውን ያነቃቃዋል፤ ስለ ብየዳም ሥራው፣ “መልካም ነው” ይለዋል፤ የጣዖቱ ምስል እንዳይወድቅም በምስማር ያጣብቀዋል።
አንሥተው በትከሻቸው ይሸከሙታል፤ እቦታው ያደርጉታል፤ በዚያም ይቆማል፤ ከዚያም ቦታ አይንቀሳቀስም፤ ማንም ወደ እርሱ ቢጮኽ አይመልስም፤ ከጭንቀቱም አያድነውም።
እግዚአብሔር የምድሪቱን አማልክት ሁሉ በሚደመስስበት ጊዜ፣ በእነርሱ ዘንድ የተፈራ ይሆናል፤ በየባሕሩ ጠረፍ የሚኖሩ ሕዝቦች፣ እያንዳንዳቸው በያሉበት ሆነው ለርሱ ይሰግዳሉ።
አገሩን በማጥፋት ላይ ባሉት ዕባጮችና ዐይጦች ዐይነት ምስሎችን ሠርታችሁ ለእስራኤል አምላክ ክብር ስጡ። ይህን ካደረጋችሁ እጁን ከእናንተ፣ ከአማልክታችሁና ከምድራችሁ ላይ ያነሣ ይሆናል።