የፈርዖንም ሹማምት፣ “ይህ ሰው እስከ መቼ ወጥመድ ይሆንብናል? አምላካቸውን እግዚአብሔርን እንዲያመልኩ ሰዎቹን ልቀቃቸውና ይሂዱ። ግብጽ መጥፋቷን እስካሁን አልተገነዘብህምን?” አሉት።
1 ሳሙኤል 5:11 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእግዚአብሔር እጅ በርትቶባቸው ስለ ነበር፣ ሞት ከተማዪቱን እጅግ አስደንግጧት ነበርና ሕዝቡ የፍልስጥኤማውያንን ገዦች በሙሉ ጠርተው፣ “የእስራኤልን አምላክ ታቦት ከዚህ አርቁልን፤ ወደ ገዛ ስፍራው ይመለስ፤ አለዚያ እኛንም ሕዝባችንንም ይፈጃል” አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእግዚአብሔር እጅ በርትቶባቸው ስለ ነበር፥ ሞት ከተማዪቱን እጅግ አስደንግጧት ነበርና ሕዝቡ የፍልስጥኤማውያንን ገዢዎች በሙሉ ጠርተው፥ “የእስራኤልን አምላክ ታቦት ከዚህ አርቁልን፤ ወደ ገዛ ስፍራው ይመለስ፤ ያለበለዚያ እኛንም ሕዝባችንንም ይፈጃል” አሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንደገና ወደ ፍልስጥኤማውያን ነገሥታት ሁሉ መልእክተኞች ልከው “እኛንና ቤተሰባችንን ሁሉ ከመፍጀቱ በፊት የእስራኤልን የቃል ኪዳን ታቦት ወደ ስፍራው መልሳችሁ ላኩ” አሉ፤ እግዚአብሔር በብርቱ ስለ ቀጣቸው በመላ ከተማይቱ የሚያስጨንቅ የሞት ፍርሀት ነበር፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልከውም የፍልስጥኤማውያንን አለቆች ሁሉ ሰብስበው፥ “የእስራኤልን አምላክ ታቦት ስደዱአት፤ እኛንና ሕዝባችንን እንዳትገድል በስፍራዋ ትቀመጥ” አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በከተማይቱ ሁሉ የሞት ድንጋጤ ነበርና፥ የእግዚአብሔርም እጅ በዚያ እጅግ ከብዳ ነበረችና ልከው የፍልስጥኤማውያንን አለቆች ሁሉ ሰብስበው፦ የእስራኤልን አምላክ ታቦት ስደዱ፥ እኛንና ሕዝባችንን እንዳይገድል ወደ ስፍራው ይመለስ አሉ። |
የፈርዖንም ሹማምት፣ “ይህ ሰው እስከ መቼ ወጥመድ ይሆንብናል? አምላካቸውን እግዚአብሔርን እንዲያመልኩ ሰዎቹን ልቀቃቸውና ይሂዱ። ግብጽ መጥፋቷን እስካሁን አልተገነዘብህምን?” አሉት።
ስለዚህ የእግዚአብሔርን ታቦት ወደ አቃሮን ሰደዱት። የእግዚአብሔር ታቦት እዚያ ሲገባም፣ የአቃሮን ሕዝብ፣ “የእስራኤልን አምላክ ታቦት ያመጡብን እኛንና ሕዝባችንን ለማስፈጀት ነው” በማለት ጮኹ።
አገሩን በማጥፋት ላይ ባሉት ዕባጮችና ዐይጦች ዐይነት ምስሎችን ሠርታችሁ ለእስራኤል አምላክ ክብር ስጡ። ይህን ካደረጋችሁ እጁን ከእናንተ፣ ከአማልክታችሁና ከምድራችሁ ላይ ያነሣ ይሆናል።