1 ሳሙኤል 3:16 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዔሊ ግን ሳሙኤልን፣ “ልጄ ሳሙኤል ሆይ” ሲል ጠራው። ሳሙኤልም፣ “እነሆኝ” ሲል መለሰ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዔሊ ግን ሳሙኤልን፥ “ልጄ ሳሙኤል ሆይ” ሲል ጠራው። ሳሙኤልም፥ “እነሆኝ” ሲል መለሰ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዔሊ ግን ሳሙኤልን “ልጄ ሳሙኤል ሆይ!” ሲል ጠራው። ሳሙኤልም “እነሆ አለሁ ጌታዬ!” ሲል መለሰ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዔሊም ሳሙኤልን ጠርቶ፥ “ልጄ ሳሙኤል ሆይ፥” አለ፤ እርሱም፥ “እነሆኝ” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዔሊም ሳሙኤልን ጠርቶ፦ ልጄ ሳሙኤል ሆይ፥ አለ፥ እርሱም፦ እነሆኝ አለ። |
እስራኤልም ዮሴፍን “እንደምታውቀው ወንድሞችህ መንጎቹን በሴኬም አካባቢ አሰማርተዋል፤ በል ተነሥ፣ ወደ እነርሱ ልላክህ።” አለው። ዮሴፍም “ይሁን ዕሺ” አለው።
ስለዚህም ቦዔዝ ሩትን፣ “ልጄ ሆይ ስሚኝ፤ ከእንግዲህ ወደ ሌላ አዝመራ ሄደሽ አትቃርሚ፤ ከዚህም አትራቂ፤ ከሴቶች ሠራተኞቼ ጋራ እዚሁ ሁኚ።
ንጉሥ ሆኖ የሚመራችሁንም ሰው እነሆ፤ አግኝታችኋል። እኔም ዕድሜዬ ገፍቷል፤ ጠጕሬም ሸብቷል፤ ልጆቼም ዐብረዋችሁ አሉ፤ ከወጣትነት ጊዜዬ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ስመራችሁ ቈይቻለሁ።
ዔሊም፣ “እግዚአብሔር የነገረህ ነገር ምንድን ነው? አትደብቀኝ፤ ከነገረህ ውስጥ አንዲቱን እንኳ ብትደብቀኝ እግዚአብሔር እንደዚያው ያድርግብህ፤ ከዚያ ለከፋም ይዳርግህ” አለው።