La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ሳሙኤል 2:36 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከዘሮችህም መካከል የተረፈው ማንኛውም ሰው፣ ለአንዲት ጥሬ ብርና ለቍራሽ እንጀራ ሲል በፊቱ ወድቆ ይሰግዳል፤ “የዕለት ጕርሴን እንዳገኝ እባክህ በማንኛውም የክህነት ሥራ ላይ መድበኝ” በማለት ይለምናል።’ ”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከቤትህም የቀረው ሁሉ ይመጣል፤ በፊቱም ሰግዶ፦ ቁራሽ እንጀራ እንድበላ ከካህናት ስፍራ ወደ አንዲቱ፥ እባክህ፥ ስደደኝ ብሎ የዕለት ምግብ ብቻ ለማግኘት ይለምናል።’”

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከአንተ ዘሮች መካከል በሕይወት የሚተርፍ ሁሉ ወደዚያ ካህን ዘንድ እየሄደ ለጥ ብሎ እጅ በመንሣት ከእርሱ ገንዘብና ምግብ ይለምናል፤ የዕለት ምግብ ብቻ ለማግኘትም ሲል ካህናትን በረዳትነት ማገልገል እንዲፈቀድለት ይለምናል።’ ”

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ከቤ​ት​ህም የቀ​ረው ሁሉ ይመ​ጣል፤ ከካ​ህ​ና​ትም ወደ አን​ዲቱ ዕጣ፥ እን​ጀራ ወደ​ም​በ​ላ​በት እባ​ክህ ላከኝ ብሎ ለአ​ንድ ብር መሐ​ልቅ ለቍ​ራሽ እን​ጀራ በፊቱ ይሰ​ግ​ዳል።”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ከቤትህም የቀረው ሁሉ ይመጣል፥ በፊቱም ሰግዶ፦ ቁራሽ እንጀራ እበላ ዘንድ ከካህናት ወደ አንዲቱ ዕጣ፥ እባክህ፥ ስደደኝ ብሎ አንድ ብር አንድ እንጀራም ይለምናል።

Ver Capítulo



1 ሳሙኤል 2:36
9 Referencias Cruzadas  

ስለዚህ እግዚአብሔር ስለ ዔሊ ቤት በሴሎ የተናገረውን ቃል ለመፈጸም፣ ሰሎሞን አብያታርን ከእግዚአብሔር ክህነት አስወገደው።


የየኰረብታው ማምለኪያ ካህናት ኢየሩሳሌም ባለው በእግዚአብሔር መሠዊያ ላይ ባያገለግሉም እንኳ ከካህናት ወንድሞቻቸው ጋራ ቂጣ ይበሉ ነበር።


ክፉዎች በደጎች ፊት፣ ኃጥኣንም በጻድቃን ደጅ ያጐነብሳሉ።


ደግሞም፣ ‘ይህ ድካም ነው’ በማለት በንቀት ጢቅ አላችሁበት” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር። “በቅሚያ የመጣውን፣ ዐንካሳውንና የታመመውን እንስሳ ቍርባን አድርጋችሁ ስታቀርቡ ከእጃችሁ መቀበል ይገባኛልን?” ይላል እግዚአብሔር፤


ሚካም፣ “እንግዲያውስ ዐብረኸኝ ተቀመጥ፤ አባትም ካህንም ሁነኝ፤ እኔም በዓመት ዐሥር ሰቅል ብር እንዲሁም ልብስና ምግብ እሰጥሃለሁ” አለው።


እንደ ልቤና እንደ አሳቤ የሚያገለግል የታመነ ካህን ለራሴ አስነሣለሁ፤ ቤቱን አጽንቼ አቆማለሁ፣ እርሱም በቀባሁት ፊት ለዘላለም ያገለግላል።


ብላቴናው ሳሙኤል ከዔሊ በታች ሆኖ እግዚአብሔርን ያገለግል ነበር። በዚያም ዘመን የእግዚአብሔር ቃል ብርቅ ነበረ፤ ራእይም አይታይም ነበር።