1 ሳሙኤል 19:1 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳኦል ዳዊትን እንዲገድሉት ለልጁ ለዮናታንና ለባልሟሎቹ ነገራቸው። ዮናታን ግን ዳዊትን እጅግ ይወድደው ነበር፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳኦል ዳዊትን እንዲገድሉት ለልጁ ለዮናታንና ለባለሟሎቹ ነገራቸው፤ ዮናታን ግን ዳዊትን እጅግ ይወደው ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሳኦል ዳዊትን ሊገድለው ማቀዱን ለልጁ ለዮናታንና ባለሟሎቹ ለሆኑት ባለሥልጣኖች ሁሉ ነገረ፤ ነገር ግን ዮናታን ዳዊትን እጅግ ይወደው ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳኦልም ለልጁ ለዮናታንና ለብላቴኖቹ ሁሉ ዳዊትን ይገድሉ ዘንድ ነገራቸው። የሳኦል ልጅ ዮናታን ግን ዳዊትን እጅግ ይወድደው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳኦልም ለልጁ ለዮናታንና ለባሪያዎቹ ሁሉ ዳዊትን ይገድሉ ዘንድ ነገራቸው። የሳኦል ልጅ ዮናታን ግን ዳዊትን እጅግ ይወድድ ነበር። |
የኢያቡስቴንም ራስ ወደ ኬብሮን ዳዊት ዘንድ አምጥተው ንጉሡን፣ “አንተን ሊገድል ይፈልግ የነበረው የጠላትህ የሳኦል ልጅ የኢያቡስቴ ራስ ይኸውልህ፤ እነሆ እግዚአብሔር በዛሬው ቀን ስለ ጌታዬ ስለ ንጉሡ ሳኦልንና ዘሩን ተበቅሏል” አሉት።
ሳኦል፣ “ዳዊትን፣ ‘ንጉሡስ ለልጅቱ ካንተ የሚፈልገው ጥሎሽ ጠላቶቹን ለመበቀል የመቶ ፍልስጥኤማውያንን ሸለፈት እንጂ ሌላ አይደለም ብላችሁ ንገሩት’ ” አላቸው። ሳኦል ይህን ያቀደው ዳዊት በፍልስጥኤማውያን እጅ እንዲወድቅ ነበር።
ሳኦል እጅግ ተቈጣ፤ ይህም ነገር አላስደሰተውም። እርሱም፣ “ለዳዊት ዐሥር ሺሕ አሉለት፤ ለእኔ ግን ሺሕ ብቻ! እንግዲህ መንግሥት እንጂ ሌላ ምን ቀረው” አለ።
እንዲህ ሲል አስጠነቀቀው፤ “አባቴ ሳኦል ሊገድልህ አጋጣሚ እየፈለገ ነው፤ ነገ ጧት ተጠንቀቅ፤ ወደ አንድ መደበቂያ ቦታም ሂድ፤ በዚያም ቈይ።
ከዚህ በኋላ ዳዊት በአርማቴም ካለችው ከነዋት ዘራማ ሸሽቶ ወደ ዮናታን በመሄድ፣ “ምን አድርጌአለሁ? ምን በደልስ ፈጸምሁ? አባትህ ሕይወቴን ለማጥፋት የሚፈልገውስ በፊቱ ምን ተገኝቶብኝ ነው?” ሲል ጠየቀው።