ሁለቱ ሰዎችም ሎጥን እንዲህ አሉት፤ “በከተማዪቱ ውስጥ የሚኖሩ የአንተ የሆኑ ሰዎች አሉህ? ዐማቾች፣ ወንዶችና ሴቶች ወይም ሌሎች ዘመዶች ካሉህ ቶሎ ብለህ ከዚህ እንዲወጡ አድርግ፤
1 ሳሙኤል 18:26 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ባለሟሎቹ ይህን ለዳዊት በነገሩት ጊዜ የንጉሥ ዐማች መሆኑ ደስ አሠኘው። ስለዚህ የተወሰነው ጊዜ ከማለፉ በፊት፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ባለሟሎቹ ይህን ለዳዊት በነገሩት ጊዜ የንጉሥ ዐማች መሆኑ ደስ አሰኘው። ስለዚህ የተወሰነው ጊዜ ከማለፉ በፊት፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሳኦል ባለሟሎችም ይህንኑ ለዳዊት ነገሩት፤ ዳዊትም የንጉሡ ዐማች እንዲሆን በመታሰቡ ደስ አለው። የሠርጉም ቀን ከመድረሱ በፊት፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሳኦልም ብላቴኖች ይህን ቃል ለዳዊት ነገሩት፤ ለንጉሥም አማች ይሆን ዘንድ ዳዊትን ደስ አሰኘው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሳኦልም ባሪያዎች ይህን ቃል ለዳዊት ነገሩት፥ ለንጉሥም አማች ይሆን ዘንድ ዳዊትን ደስ አሰኘው። |
ሁለቱ ሰዎችም ሎጥን እንዲህ አሉት፤ “በከተማዪቱ ውስጥ የሚኖሩ የአንተ የሆኑ ሰዎች አሉህ? ዐማቾች፣ ወንዶችና ሴቶች ወይም ሌሎች ዘመዶች ካሉህ ቶሎ ብለህ ከዚህ እንዲወጡ አድርግ፤
ሳኦልም በልቡ፣ “ወጥመድ እንድትሆነው፣ በፍልስጥኤማውያንም እጅ እንዲጠፋ እርሷን እድርለታለሁ” ሲል ዐሰበ። ስለዚህ ሳኦል ዳዊትን፣ “እነሆ፤ ዛሬ ለሁለተኛ ጊዜ ዐማቼ ትሆናለህ” አለው።