1 ሳሙኤል 15:5 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳኦልም ወደ አማሌቅ ከተማ ሄዶ በአንዲት ሸለቆ ውስጥ አደፈጠ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳኦልም ወደ አማሌቅ ከተማ ሄዶ በሸለቆ ውስጥ አደፈጠ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያም እርሱና ሠራዊቱ ወደ ዐማሌቃውያን ከተማ ሄደው በአንድ ደረቅ ጅረት ውስጥ ደፈጣ አደረጉ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳኦልም ወደ አማሌቅ ከተማ ወጣ፤ በሸለቆውም ውስጥ ተደበቀ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳኦልም ወደ አማሌቅ ከተማ ወጣ፥ በሸለቆውም ውስጥ ተደበቀ። |
ስለዚህ ሳኦል ሰዎቹን ጥላኢም በተባለ ቦታ ሰብስቦ ቈጠራቸው፤ እነርሱም ሁለት መቶ ሺሕ እግረኛ ወታደሮችና ከይሁዳም ዐሥር ሺሕ ሰዎች ነበሩ፤
እርሱም፣ ቄናውያንን፣ “ከእነርሱ ጋራ እንዳላጠፋችሁ ከአማሌቃውያን ራቁ፤ ተለዩአቸውም፤ እስራኤላውያን ከግብጽ ምድር በወጡ ጊዜ፣ ቸርነት አድርጋችሁላቸዋልና” አላቸው። ስለዚህ ቄናውያን ከአማሌቃውያን ተለዩ።