አኪያም የእግሯን ኮቴ ድምፅ እበሩ ላይ እንደ ሰማ እንዲህ አላት፤ “የኢዮርብዓም ሚስት ሆይ ግቢ፤ ግን ለምንድን ነው ሌላ ሴት መስለሽ ለመታየት የፈለግሽው? ለአንቺ ከባድ ነገር እንድነግርሽ ተልኬአለሁ።
1 ሳሙኤል 15:16 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳሙኤልም ሳኦልን፣ “ስማ! ትናንት ማታ እግዚአብሔር የነገረኝን ልንገርህ?” አለው። ሳኦልም፣ “ንገረኝ” ሲል መለሰለት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳሙኤልም ሳኦልን፥ “ስማ! ትናንት ማታ ጌታ የነገረኝን ልንገርህ?” አለው። ሳኦልም፥ “ንገረኝ” ሲል መለሰለት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሳሙኤልም “ተወው በቃ፤ እግዚአብሔር ትናንትና ማታ የገለጠልኝን እነግርሃለሁ” አለው። ሳኦልም “እሺ ንገረኝ” አለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳሙኤልም ሳኦልን፥ “ስማ፤ እግዚአብሔር ዛሬ ሌሊት የነገረኝን ልንገርህ” አለው፤ እርሱም፥ “ተናገር” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳሙኤልም ሳኦልን፦ ቆይ፥ እግዚአብሔር ዛሬ ሌሊት የነገረኝን ልንገርህ አለው፥ እርሱም፦ ተናገር አለው። |
አኪያም የእግሯን ኮቴ ድምፅ እበሩ ላይ እንደ ሰማ እንዲህ አላት፤ “የኢዮርብዓም ሚስት ሆይ ግቢ፤ ግን ለምንድን ነው ሌላ ሴት መስለሽ ለመታየት የፈለግሽው? ለአንቺ ከባድ ነገር እንድነግርሽ ተልኬአለሁ።
ሳኦልም፣ “ሰራዊቱ ከአማሌቃውያን ማርከው ያመጧቸው ናቸው፤ ምርጥ ምርጦቹ በጎችና በሬዎች ለእግዚአብሔር ለአምላክህ መሥዋዕት እንዲሆኑ ሳይገድሉ የተዉአቸው ናቸው፤ የቀሩትን ግን በሙሉ አጥፍተናል” ብሎ መለሰ።
ሳሙኤልም እንዲህ አለው፤ “በዐይንህ ፊት ታናሽ የነበርህ ብትሆንም፣ የእስራኤል ነገዶች መሪ ሆነህ የለምን? እግዚአብሔርም በእስራኤል ላይ ቀብቶ አንግሦሃል።
ወደ ከተማዪቱ ዳርቻ እየወረዱ ሳለ፣ ሳሙኤል ሳኦልን፣ “አገልጋይህ ወደ ፊት ቀድሞን እንዲሄድ ንገረው” አለው፤ አገልጋዩም እንደ ተነገረው አደረገ፤ ከዚህ በኋላ ሳሙኤል፣ “አንተ ግን ከእግዚአብሔር የተላከ መልእክት እነግርህ ዘንድ ለጥቂት ጊዜ እዚህ ቈይ” አለው።