1 ሳሙኤል 1:28 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ እኔም ለእግዚአብሔር እሰጠዋለሁ፤ በሕይወት ዘመኑም ሁሉ ለእግዚአብሔር የተሰጠ ይሆናል።” እርሱም በዚያ ለእግዚአብሔር ሰገደ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ እኔም ለጌታ እሰጠዋለሁ፤ በሕይወት ዘመኑም ሁሉ ለጌታ የተሰጠ ይሆናል።” እርሱም በዚያ ለጌታ ሰገደ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔም ደግሞ እርሱን ለእግዚአብሔር የተለየ ስጦታ እንዲሆን አድርጌአለሁ፤ ስለዚህም በሕይወቱ ዘመን ሁሉ ለእግዚአብሔር የተሰጠ ይሆናል።” ከዚያም በኋላ በዚያ ለእግዚአብሔር ሰገዱ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔም ደግሞ ዕድሜውን ሙሉ እግዚአብሔርን ያገለግል ዘንድ ለእግዚአብሔር ሰጥቼዋለሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም የለመንሁትን ልመናዬን ሰጥቶኛል፥ እኔም ደግሞ ለእግዚአብሔር ሰጥቼዋለሁ፥ ዕድሜውን ሁሉ ለእግዚአብሔር የተሰጠ ይሆናል። |
ተደፍቼም ለእግዚአብሔር ሰገድሁ፤ ለጌታዬ ወንድም የልጅ ልጅ የሆነችውን ቈንጆ፣ ለጌታዬ ልጅ እንዳገኝለት በቀና መንገድ የመራኝን የጌታዬ የአብርሃምን አምላክ እግዚአብሔርን አመሰገንሁ።
ጌዴዎንም ሕልሙንና ፍችውን በሰማ ጊዜ ሰገደ፤ ከዚያም ወደ እስራኤላውያን ሰፈር ወጥቶ፣ “እግዚአብሔር የምድያማውያንን ሰፈር በእጃችሁ አሳልፎ ሰጥቷልና ተነሡ” አላቸው።
እንዲህም ብላ ስእለት ተሳለች፤ “የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ የአገልጋይህን መዋረድ ተመልክተህ ብታስበኝና አገልጋይህን ሳትረሳት ወንድ ልጅ ብትሰጣት፣ በሕይወት ዘመኑ ሁሉ ለእግዚአብሔር እሰጠዋለሁ፤ ምላጭም በራሱ ላይ አይደርስም።”
ሐና ግን አልሄደችም፤ እርሷም ባሏን፣ “ሕፃኑ ጡት ከተወ በኋላ፣ ወስጄ በእግዚአብሔር ፊት አቀርበዋለሁ፤ እስከ ሕይወቱ ፍጻሜም በዚያ ይኖራል” አለችው።
ዔሊም፣ “በጸሎት ባገኘችውና ለእግዚአብሔር በሰጠችው ልጅ ምትክ እግዚአብሔር ከዚህችው ሴት ዘር ይስጥህ” እያለ ሕልቃናንና ሚስቱን ይመርቃቸው ነበር፤ ከዚያ በኋላ ወደ ቤታቸው ይመለሱ ነበር።
ዳዊትም፣ “አገልጋይህ ምን እንደሚያደርግ ያን ጊዜ አንተው ራስህ ታያለህ” አለው። አንኩስም፣ “መልካም፤ በዘመኔ ሁሉ የራሴ የክብር ዘብ አደርግሃለሁ” ሲል መለሰለት።