1 ሳሙኤል 1:12 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሐና ባለማቋረጥ ወደ እግዚአብሔር በጸለየች ጊዜ፣ ዔሊ አፏን ይመለከት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጸሎትዋንም ባለማቋረጥ ወደ ጌታ ባቀረበች ጊዜ፥ ዔሊ አፏን ይመለከት ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሐና በዚህ ዐይነት ጸሎትዋን በማስረዘም ብዙ ጊዜ ስለ ቈየች፥ ዔሊ አፍዋን ይመለከት ነበር፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጸሎቷንም በእግዚአብሔር ፊት ባበዛች ጊዜ፥ ካህኑ ዔሊ አፍዋን ይመለከት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጸሎትዋንም በእግዚአብሔር ፊት ባበዛች ጊዜ ዔሊ አፍዋን ይመለከት ነበር። |
ስለዚህ ኀጢአታችሁን እርስ በርሳችሁ ተናዘዙ፤ ትፈወሱም ዘንድ አንዱ ለሌላው ይጸልይ። የጻድቅ ሰው ጸሎት ኀይል አለው፤ ታላቅ ነገርም ያደርጋል።
እንዲህም ብላ ስእለት ተሳለች፤ “የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ የአገልጋይህን መዋረድ ተመልክተህ ብታስበኝና አገልጋይህን ሳትረሳት ወንድ ልጅ ብትሰጣት፣ በሕይወት ዘመኑ ሁሉ ለእግዚአብሔር እሰጠዋለሁ፤ ምላጭም በራሱ ላይ አይደርስም።”