1 ጴጥሮስ 2:6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምክንያቱም በመጽሐፍ እንዲህ ተብሎ ተጽፏልና፤ “እነሆ፤ የተመረጠና የከበረ የማእዘን ድንጋይ፣ በጽዮን አኖራለሁ፤ በርሱም የሚያምን ፈጽሞ አያፍርም።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምክንያቱም በመጽሐፍ “እነሆ፥ የተመረጠና ክቡር የማእዘን ድንጋይ፥ በጽዮን አኖራለሁ፤ በእርሱም የሚያምን አያፍርም፤” ተብሎ ተጽፎአልና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በቅዱስ መጽሐፍ “እነሆ! የተመረጠና ክቡር የሆነ የማእዘን ድንጋይ በጽዮን አኖራለሁ፤ በእርሱም የሚያምን አያፍርም” የሚል ቃል ተጽፎ ይገኛል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመጽሐፍ “እነሆ የተመረጠና የከበረን የማዕዘን ራስ ድንጋይ በጽዮን አኖራለሁ፤ በእርሱም የሚያምን አያፍርም፤” ተብሎ ተጽፎአልና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በመጽሐፍ፦ እነሆ፥ የተመረጠና የከበረን የማዕዘን ራስ ድንጋይ በጽዮን አኖራለሁ በእርሱም የሚያምን አያፍርም ተብሎ ተጽፎአልና። |
በዚያ ጊዜ በራእይ ተናገርህ፤ ታማኝ ሕዝብህንም እንዲህ አልህ፤ “ኀያሉን ሰው ሥልጣን አጐናጸፍሁት፤ ከሕዝብ መካከል የተመረጠውንም ከፍ ከፍ አደረግሁት።
ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እነሆ፤ የተፈተነ ድንጋይ፣ የመሠረት ድንጋይ፣ ለጽኑ መሠረት የሚሆን የከበረ የማእዘን ድንጋይ፣ በጽዮን አኖራለሁ፤ በርሱም የሚያምን አያፍርም።
“አይዞሽ አትፍሪ፤ ኀፍረት አይገጥምሽም፤ ውርደት ስለማይደርስብሽ አትሸማቀቂ፤ የወጣትነት ኀፍረትሽን ትረሺዋለሽ፤ የመበለትነት ስድብሽንም ከእንግዲህ አታስታውሺውም።
አስቀድሜ ግን በእውነት መጽሐፍ ውስጥ የተጻፈውን እነግርሃለሁ፤ ከእነዚህ አለቆች ጋራ ለመዋጋት ከአለቃችሁ ከሚካኤል በቀር የሚረዳኝ የለም።”
ኢየሱስም ወደ እነርሱ ተመልክቶ እንዲህ አላቸው፤ “ ‘ታዲያ ግንበኞች የናቁት ድንጋይ፣ እርሱ የማእዘን ራስ ሆነ’ ተብሎ የተጻፈው ትርጕሙ ምንድን ነው?
ሕዝቡም ቆመው ይመለከቱ ነበር። ገዦችም፣ “ሌሎችን አዳነ፤ በእግዚአብሔር የተመረጠው ክርስቶስ እርሱ ከሆነ፣ እስኪ ራሱን ያድን” እያሉ አፌዙበት።
እንዲህ አለ፤ “ወንድሞች ሆይ፤ ኢየሱስን ለያዙት ሰዎች መሪ ስለ ሆናቸው ስለ ይሁዳ፣ መንፈስ ቅዱስ አስቀድሞ በዳዊት አፍ የተናገረው የመጽሐፉ ቃል መፈጸም ስላለበት፣
እርሱ ስለ እነዚህ ነገሮች በመልእክቶቹ ሁሉ ጽፏል፤ በመልእክቶቹም ውስጥ በቀላሉ ለመረዳት የሚያዳግቱ ነገሮች አሉ። ዕውቀት የጐደላቸውና ጽናት የሌላቸው ሰዎች ሌሎችን ቅዱሳት መጻሕፍት እንደሚያጣምሙ፣ እነዚህንም ደግሞ ለገዛ ጥፋታቸው ያጣምማሉ።