ያዕቆብም፣ “ልጄ ዐብሯችሁ ወደዚያ አይወርድም፤ ወንድሙ እንደሆን ሞቷል፤ የቀረው እርሱ ብቻ ነው። ይዛችሁት ስትሄዱ በመንገድ ላይ አደጋ ቢደርስበት፣ ሽበቴን በመሪር ሐዘን ወደ መቃብር ታወርዱታላችሁ” አላቸው።
1 ነገሥት 2:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሁን ግን በደል እንደሌለበት ሰው አትተወው፤ ጥበበኛ ነህና መደረግ ያለበትን ታውቃለህ፤ ሽበቱን በደም ወደ መቃብር አውርድ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንተ ግን እርሱንም ከቅጣት ነጻ አታድርገው፤ ባለህ ጥበብ ምን መደረግ እንዳለበት አንተ ራስህ ታውቃለህ፤ በሞት የሚቀጣ መሆኑንም አትዘንጋ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንተ ግን እርሱንም ከቅጣት ነጻ አታድርገው፤ ባለህ ጥበብ ምን መደረግ እንዳለበት አንተ ራስህ ታውቃለህ፤ በሞት የሚቀጣ መሆኑንም አትዘንጋ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንተ ግን ጥበበኛ ሰው ነህና ንጹሕ አታድርገው፤ የምታደርግበትንም አንተ ታውቃለህ፤ ሽበቱንም በደም ወደ መቃብር አውርደው” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንተ ግን ጥበበኛ ሰው ነህና ያለ ቅጣት አትተወው፤ የምታደርግበትንም አንተ ታውቃለህ፤ ሽበቱንም ከደም ጋር ወደ መቃብር አውርድ።” |
ያዕቆብም፣ “ልጄ ዐብሯችሁ ወደዚያ አይወርድም፤ ወንድሙ እንደሆን ሞቷል፤ የቀረው እርሱ ብቻ ነው። ይዛችሁት ስትሄዱ በመንገድ ላይ አደጋ ቢደርስበት፣ ሽበቴን በመሪር ሐዘን ወደ መቃብር ታወርዱታላችሁ” አላቸው።
የልጁን ከእኛ ጋራ አለመኖር ሲያይ አባቴ ይሞታል። ከዚህም የተነሣ እኛ አገልጋዮችህ የአባታችንን ሽበት በመሪር ሐዘን ወደ መቃብር እናወርደዋለን።
ምንም እንኳ ዛሬ የተቀባሁ ንጉሥ ብሆንም፣ እኔ ደካማ ሰው ነኝ፤ እነዚህ የጽሩያ ልጆች እጅግ በርትተውብኛል። እግዚአብሔር ለክፉ አድራጊ የእጁን ይስጠው።”