ዘካርያስ 6:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ መልአኩ “ወደ ሰሜን አገሮች የሄዱት ፈረሶች የእግዚአብሔርን ቊጣ እንዲበርድ አደረጉ” ሲል ወደ እኔ ጮኸ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ጮኾ እንዲህ አለኝ፤ “እነሆ፤ ወደ ሰሜን አገር የሚወጡት፣ መንፈሴን በሰሜን ምድር አሳርፈውታል።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም ጮኾ፦ “እነሆ፥ ወደ ሰሜን ምድር የሚወጡት እነርሱ መንፈሴን በሰሜን ምድር ላይ አሳርፈዋል” በማለት ተናገረኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጮኾም፦ እነሆ፥ ወደ ሰሜን ምድር የሚወጡት እነርሱ መንፈሴን በሰሜን ምድር ላይ አሳርፈዋል ብሎ ተናገረኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጮኾም፦ እነሆ፥ ወደ ሰሜን ምድር የሚወጡት እነርሱ መንፈሴን በሰሜን ምድር ላይ አሳርፈዋል ብሎ ተናገረኝ። |
“ሁላችሁም ተሰብስባችሁ ኑና አድምጡ! ስለ እነዚህ ነገሮች አስቀድሞ የተናገረ ከጣዖቶች መካከል የትኛው ነው? የእግዚአብሔር ተመራጭ በባቢሎን ላይ ዓላማውን ይፈጽማል። ኀይሉም በባቢሎናውያን ላይ ይሆናል።
ይህንንም የማደርገው፥ ለፈጸምሽው በደል ሁሉ ይቅርታ ሳደርግልሽ ሥራሽን በማስታወስ በድንጋጤ ዐፍረሽ ጸጥ እንድትዪ ነው፤” ይህን የተናገረ ልዑል እግዚአብሔር ነው።
ኢየሩሳሌም ሆይ! ሴሰኛነትሽ አርክሶሻል፤ እኔ እንኳ ላነጻሽ ብፈቅድ አንቺ ከርኲሰትሽ አልነጻሽም። የቊጣዬ ኀይል እስከሚገለጥብሽ ድረስ ዳግመኛ ንጹሕ አትሆኚም።
“ቊጣዬ በእርሱ ላይ ይፈጸማል ኀይለኛ ቊጣዬንም በእነርሱ ላይ አውርጄ እረካለሁ ይህንንም ቊጣዬን በእነርሱ ላይ ባወረድኩ ጊዜ እኔ እግዚአብሔር በቅናቴ የተናገርኩ መሆኔን ያውቃሉ።
ሰላም አግኝተው በጸጥታ በሚኖሩ በአሕዛብ መንግሥታት ላይ እጅግ ተቈጥቼአለሁ፤ ምክንያቱም እኔ ሕዝቤን ከመቅጣት መለስ ባልኩበት ጊዜ እነዚያ የአሕዛብ መንግሥታት ሕዝቤን ከተጠበቀው በላይ አሠቃይተዋል።
እግዚአብሔር የምድያማውያንን መሪዎች ገድላችሁ ድልን እንድትቀዳጁ አድርጓችኋል። ታዲያ እኔ ከዚህ ጋር የሚወዳደር ምን ሠራሁ?” እርሱም ይህን ባለ ጊዜ ቊጣቸው በረደ።