የእግዚአብሔር መሠዊያ የሆነችውን ከተማ ለማጥቃት የሚመጡ የመንግሥታት ሠራዊቶች ሁሉ ከነጦር መሣሪያዎቻቸው ይደመሰሳሉ፤ እንደ ሕልም ወይም በእንቅልፍ ልብ እንደሚታሰብ ነገር የተረሱ ይሆናሉ።
ዘካርያስ 12:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ጊዜ በኢየሩሳሌም ላይ በጠላትነት የሚነሡትን የአሕዛብ መንግሥታት ሁሉ ለመደምሰስ እነሣለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ቀን ኢየሩሳሌምን በወጓት አሕዛብ ሁሉ ላይ እወጣለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያም ቀን በኢየሩሳሌም ላይ የሚነሡትን አሕዛብ ሁሉ ለማጥፋት እፈልጋለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያም ቀን በኢየሩሳሌም ላይ የሚመጡትን አሕዛብ ሁሉ ለማጥፋት እጋደላለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያም ቀን በኢየሩሳሌም ላይ የሚመጡትን አሕዛብ ሁሉ ለማጥፋት እጋደላለሁ። |
የእግዚአብሔር መሠዊያ የሆነችውን ከተማ ለማጥቃት የሚመጡ የመንግሥታት ሠራዊቶች ሁሉ ከነጦር መሣሪያዎቻቸው ይደመሰሳሉ፤ እንደ ሕልም ወይም በእንቅልፍ ልብ እንደሚታሰብ ነገር የተረሱ ይሆናሉ።
አንቺን ለማጥፋት የሚሠራ መሣሪያ ዘላቂነት አይኖረውም፤ ለሚከሱሽ ሁሉ በቂ መልስ ይኖርሻል፤ የእኔ አገልጋዮች ርስትና ከእኔ የሚፈረድላቸው ፍርድ ይህ ነው፤” ይላል እግዚአብሔር።
በዚያን ጊዜ፥ የመንግሥታትን ዙፋን እገለብጣለሁ፤ ኀይላቸውንም እንዳልነበረ አደርጋለሁ፤ ሠረገላ ነጂዎችን ከነሠረገሎቻቸው እገለብጣለሁ፤ ፈረሶቻቸው ያልቃሉ፤ ፈረሰኞቻቸውም እርስ በርሳቸው ይጋደላሉ፤
“ኢየሩሳሌምን በዙሪያዋ ላሉ ሕዝቦች ጠጥተውት እንደሚያንገዳግድ የወይን ጠጅ ዋንጫ አደርጋታለሁ፤ እነርሱ ኢየሩሳሌምን በሚይዙ ጊዜ የቀሩትም የይሁዳ ከተሞች ይከበባሉ።