ዘካርያስ 1:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምድርን ተዘዋውረው ይቃኙ ዘንድ እግዚአብሔር የላካቸው ናቸው” አለኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም በባርሰነት ዛፎች መካከል የቆመው ሰው፣ “እነዚህ በምድር ሁሉ እንዲመላለሱ እግዚአብሔር የላካቸው ናቸው” ሲል መለሰ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በባርሰነት ዛፎች መካከልም ቆሞ የነበረው ሰው፦ “እነዚህ ምድርን እንዲያስሱ ጌታ የላካቸው ናቸው” ብሎ መለሰ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በባርሰነት ዛፎች መካከልም ቆሞ የነበረው ሰው፦ እነዚህ በምድር ላይ ይመላለሱ ዘንድ እግዚአብሔር የላካቸው ናቸው ብሎ መለሰ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በባርሰነት ዛፎች መካከልም ቆሞ የነበረው ሰው፦ እነዚህ በምድር ላይ ይመላለሱ ዘንድ እግዚአብሔር የላካቸው ናቸው ብሎ መለሰ። |
የእግዚአብሔር መልአክ በቀይ ፈረስ ላይ ተቀምጦ አየሁ። እርሱም በሸለቆው ውስጥ ባሉ በባርሰነት ዛፎች መካከል ቆመ፤ በስተኋላውም ቀይ፥ ሐመርና አምባላይ ፈረሶች ይከተሉት ነበር።
የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ “ሰይፍ ሆይ! ተባባሪዬ በሆነው በእረኛዬ ላይ ንቃ! በጎቹ ይበተኑ ዘንድ እረኛውን ምታ! እኔም በታናናሾቹ ላይ እጄን አነሣለሁ።
ትንሽ ነገር የሚደረግበትን ቀን የናቀ ቱምቢውን በዘሩባቤል እጅ ሲያይ ይደሰታል፤ እነዚህ ሰባቱ መቅረዞች ዓለምን የሚያካልሉ የእግዚአብሔር ዐይኖች ናቸው።”