ማንኛይቱም ባል የሞተባት ሴት ልጆች ወይም የልጅ ልጆች ቢኖሩአት እነዚህ ልጆች አስቀድመው ለቤተሰቦቻቸው የመጠንቀቅን፥ ለወላጆቻቸውና ለአያቶቻቸው ብድር የመመለስን መንፈሳዊ ግዴታ ይማሩ፤ ይህ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ነገር ነው።
ሩት 2:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እህሉንም ተሸክማ ወደ ከተማ ተመለሰች፤ ምን ያኽል እንደ ሰበሰበችም ለዐማትዋ አሳየቻት፤ ከምሳዋ ተርፎአት የነበረውንም ምግብ ሰጠቻት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያንም ይዛ ወደ ከተማ ሄደች፤ ዐማቷም የሰበሰበችው ምን ያህል እንደ ሆነም አየች፤ እንዲሁም ሩት የሚበቃትን ያህል ከበላች በኋላ አስተርፋ የነበረውን አውጥታ ለርሷ ሰጠቻት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ተሸክማውም ወደ ከተማ ገባች፥ አማትዋም የቃረመችውን አየች፥ ከጠገበችም በኋላ የተረፋትን አውጥታ ሰጠቻት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ተሸክማውም ወደ ከተማ ገባች፥ አማትዋም የቃረመችውን አየች፣ ከጠገበችም በኋላ የተረፋትን አውጥታ ሰጠቻት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ተሸክማውም ወደ ከተማ ገባች፤ አማትዋም የቃረመችውን አየች፤ ከጠገበችም በኋላ የተረፋትን አውጥታ ሰጠቻት። |
ማንኛይቱም ባል የሞተባት ሴት ልጆች ወይም የልጅ ልጆች ቢኖሩአት እነዚህ ልጆች አስቀድመው ለቤተሰቦቻቸው የመጠንቀቅን፥ ለወላጆቻቸውና ለአያቶቻቸው ብድር የመመለስን መንፈሳዊ ግዴታ ይማሩ፤ ይህ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ነገር ነው።
በምሳ ሰዓት ቦዔዝ ሩትን “ነይ ወደ ገበታው ቅረቢ፤ በወጡም እያጠቀስሽ እንጀራ ብዪ” አላት። እርስዋም ከአጫጆቹ ጋር ተቀመጠች፤ ቦዔዝም የተጠበሰ እሸት ሰጣት፤ እስክትጠግብ ድረስ በላች፤ ምግብም ተርፏት ነበር።