ሩት 1:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ሁለቱም አብረው ወደ ቤተልሔም ተጓዙ፤ ቤተልሔም ሲደርሱም የከተማው ሰዎች ሁሉ ተገረሙ፤ እዚያም ያሉ ሴቶች በመደነቅ “በእርግጥ ይህች ናዖሚ ናትን?” አሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ሁለቱ ሴቶች እስከ ቤተ ልሔም ድረስ ተጓዙ፤ ቤተ ልሔም እንደ ደረሱም፣ በእነርሱ ምክንያት ከተማው በሙሉ ተተረማመሰ፤ ሴቶቹም፣ “ይህች ኑኃሚን ናትን?” በማለት ተገረሙ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ሁለቱም እስከ ቤተልሔም ድረስ ሄዱ። ወደ ቤተልሔምም በደረሱ ጊዜ፥ ያገሩ ሰዎች ሁሉ ታወኩ ስለ እነርሱ፥ ሴቶቹም፦ “ይህች ናዖሚን ናትን?” አሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሁለቱም እስከ ቤተ ልሔም ድረስ ሄዱ። ወደ ቤተ ልሔምም በደረሱ ጊዜ የከተማይቱ ሰዎች ሁሉ ስለ እነርሱ፦ ይህች ኑኃሚን ናትን? እያሉ ተንጫጩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሁለቱም እስከ ቤተ ልሔም ድረስ ሄዱ። ወደ ቤተ ልሔምም በደረሱ ጊዜ የከተማይቱ ሰዎች ሁሉ ስለ እነርሱ “ይህች ኑኃሚን ናትን?” እያሉ ተንጫጩ። |
“ፍጹም ውብ ናት የሚሏት የዓለም መደሰቻ የነበረችው ከተማ ይህች ናትን?” እያሉ በመንገድ የሚያልፉ ሁሉ በኢየሩሳሌም ላይ እጃቸውን እያጨበጨቡ ራሳቸውን በመነቅነቅ አሽሟጠጡ።