ሩት 1:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሩት ከእርስዋ ጋር ለመሄድ ቊርጥ ሐሳብ ማድረጓን በተረዳች ጊዜ፥ ናዖሚ ሌላ ነገር አልተናገረችም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሩት ዐብራት ለመሄድ መቍረጧን በተረዳች ጊዜ፣ ኑኃሚን መጐትጐቷን ተወች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእርሷ ጋር ለመሄድ እንደ ቈረጠች ባየች ጊዜ ናዖሚ ከመናገር ዝም አለች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኑኃሚንም ከእርስዋ ጋር ለመሄድ እንደ ቈረጠች ባየች ጊዜ እርስዋን ከመናገር ዝም አለች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኑኃሚንም ከእርስዋ ጋር ለመሄድ እንደ ቈረጠች ባየች ጊዜ እርስዋን ከመናገር ዝም አለች። |
ስለዚህ ሁለቱም አብረው ወደ ቤተልሔም ተጓዙ፤ ቤተልሔም ሲደርሱም የከተማው ሰዎች ሁሉ ተገረሙ፤ እዚያም ያሉ ሴቶች በመደነቅ “በእርግጥ ይህች ናዖሚ ናትን?” አሉ።