ሮሜ 16:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በጌታ ለምወደው ለአምጵልያቶስ ሰላምታ አቅርቡልኝ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በጌታ ለምወድደው ለጵልያጦን ሰላምታ አቅርቡልኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጌታ ለምወደው ለአምፕሊያቶን ሰላምታ አቅርቡልኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በክርስቶስ ወንድሜ የሆነውን አምጵልያጦስን ሰላም በሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በጌታ ለምወደው ለጵልያጦን ሰላምታ አቅርቡልኝ። |
በእነርሱ ቤት ለጸሎት ለሚሰበሰቡት ምእመናንም ሰላምታ አቅርቡልኝ። በእስያ ክፍለ ሀገር በመጀመሪያ በክርስቶስ ላመነውና ለምወደው ለኤጴኔጦስ ሰላምታ አቅርቡልኝ።
ከእኔ ጋር ታስረው ለነበሩና በሐዋርያትም መካከል ታዋቂዎች ለነበሩት አይሁድ ዘመዶቼ፥ ለአንድሮኒቆስና ለዩኒያስ ሰላምታ አቅርቡልኝ፤ እነርሱ በክርስቶስ በማመን እኔን ይቀድሙኛል።