ሮሜ 15:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንደገናም፦ “አሕዛብ ሁሉ! ጌታን አመስግኑት፤ ሕዝቦች ሁሉ አመስግኑት!” ተብሎ ተጽፎአል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንደ ገናም፣ “አሕዛብም ሁላችሁ ጌታን አመስግኑት፤ ሕዝቦችም ሁሉ ወድሱት” ይላል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንደገናም “አሕዛብ ሁላችሁ! ጌታን አመስግኑ፤ ሕዝቦቹም ሁሉ ያመስግኑት፤” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳግመናም እንዲህ አለ፥ “አሕዛብ ሁላችሁ እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ሕዝቡም ሁሉ ያመሰግኑታል።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደግሞም፦ እናንተ አሕዛብ ሁላችሁ፥ ጌታን አመስግኑ ሕዝቦቹም ሁሉ ይወድሱት ይላል። |
እንዲሁም ኢሳይያስ፦ “ከእሴይ ዘር የሚወለድ ይመጣል፤ የአሕዛብም መሪ ለመሆን ይነሣል፤ እነርሱም ተስፋቸውን በእርሱ ላይ ያደርጋሉ” ይላል።