ሮሜ 11:31 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ ምሕረትን ባገኛችሁበት ዐይነት እነርሱም ምሕረትን እንዲያገኙ እነርሱ አሁን ለእግዚአብሔር የማይታዘዙ ሆነዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ለእናንተ ምሕረት ከማድረጉ የተነሣ፣ እነርሱም ምሕረት ያገኙ ዘንድ አሁን የማይታዘዙ ልጆች ሆነዋል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲሁም እናንተ ያገኛችሁትን ምሕረት፥ እነርሱ ደግሞ ምሕረትን እንዲያገኙ፥ እነዚህ ደግሞ አሁን አልታዘዙም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲሁም እናንተ በተማራችሁት ምሕረት እነርሱ ምሕረትን እንዲያገኙ እነርሱ ዛሬ አልታዘዙትም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲሁ በተማራችሁበት ምሕረት እነርሱ ደግሞ ምሕረትን ያገኙ ዘንድ እነዚህ ደግሞ አሁን አልታዘዙም። |
እግዚአብሔር እነርሱን በጣላቸው ጊዜ ሌላው የዓለም ሕዝብ ከእግዚአብሔር ጋር ከታረቀ እግዚአብሔር እነርሱን በሚቀበላቸው ጊዜ ምን የሚሆን ይመስላችኋል? ይህማ ከሞት እንደ መነሣት ያኽል ነው!
ወንድሞቼ ሆይ! “ዐዋቂዎች ነን” ብላችሁ አትመኩ፤ የምነግራችሁ አንድ ምሥጢር አለ፤ ይኸውም የእስራኤላውያን እምቢተኛነት ለዘለቄታው ሳይሆን አሕዛብ ሁሉ በሙላት ወደ እግዚአብሔር እስኪመጡ ድረስ መሆኑን ነው።
እናንተ አሕዛብ ቀድሞ ለእግዚአብሔር የማትታዘዙ ነበራችሁ፤ አሁን ግን አይሁድ ባለመታዘዛቸው ምክንያት እናንተ የእግዚአብሔርን ምሕረት አገኛችሁ።