መዝሙር 83:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱ “የእግዚአብሔርን ሕዝብ ርስት የራሳችን እናደርጋለን” ብለው ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነዚህም፣ “የእግዚአብሔርን የግጦሽ ቦታ፣ ወስደን የግላችን እናድርግ” የሚሉ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አለቆቻቸውን እንደ ሔሬብና እንደ ዜብ፥ ታላላቆቻቸውንም እንደ ዛብሄልና እንደ ስልማና አድርጋቸው፦ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤቱ የኀያላን አምላክ ሆይ፥ በአንተ የታመነ ሰው ብፁዕ ነው። |
ዖሬብና ዘኤብ የተባሉ ሁለት የምድያማውያን መሪዎችንም ማረኩ፤ ዖሬብን “የዖሬብ አለት” ተብሎ ወደሚጠራው ስፍራ፥ ዘኤብንም “የዘኤብ የወይን መጭመቂያ” ተብሎ በሚጠራው ቦታ ገደሉአቸው፤ ከዚህም በኋላ የቀሩትን ምድያማውያን ማሳደድ ቀጠሉ፤ የዖሬብንና የዘኤብንም ራሶች ቈርጠው ወደ ጌዴዎን አመጡለት፤ በዚያን ጊዜ ጌዴዎን ከዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ በኩል ነበረ።
ከዚህ በኋላ ዜባሕና ጻልሙናዕ ጌዴዎንን “በል እንግዲህ አንተው ራስህ ግደለን፤ የሰው ኀይሉ እንደ ሰውነቱ ነው” አሉት፤ ስለዚህ ጌዴዎን እነርሱን ገድሎ በግመሎቻቸው አንገት ላይ የነበረውን ጌጣጌጥ በሙሉ ወሰደ።