መዝሙር 68:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ትእዛዝ ሰጠ፤ ብዙ ሴቶችም ዜናውን አሠራጩ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጌታ እንዲህ ሲል ቃሉን አስተላለፈ፤ ትእዛዙን የሚያውጁትም ብዙ ሰራዊት ናቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንስሶችህ በውስጡ አደሩ፥ አቤቱ፥ በቸርነትህ ለድሆች አዘጋጀህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ማቅ ለበስሁ መተረቻም ሆንሁላቸው። |
እርሱም አንዳንዶቹ ሐዋርያት፥ አንዳንዶቹ ነቢያት፥ አንዳንዶቹ የወንጌል ሰባኪዎች፥ አንዳንዶቹ የምእመናን እረኞች፥ አንዳንዶቹ አስተማሪዎች እንዲሆኑ ስጦታዎችን ሰጣቸው።
የአቢኒዓምን ልጅ ባራቅን የንፍታሌም ድርሻ ከሆነችው ከቃዴስ ከተማ አስጠርታ እንዲህ አለችው፤ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይህን ትእዛዝ ሰጥቶሃል፦ ‘ከንፍታሌምና ከዛብሎን ነገዶች ዐሥር ሺህ ሰዎች መርጠህ ወደ ታቦር ተራራ ውሰዳቸው፤
ዳዊት ጎልያድን ገድሎ ሲመለስና ወታደሮችም ወደየቤታቸው በማምራት ላይ ሳሉ፥ በእስራኤል በሚገኙት ከተሞች ሁሉ የሚኖሩ ሴቶች ሳኦልን ለመቀበል ወጡ፤ እነርሱም በእልልታ እየዘፈኑና እየጨፈሩ፥ የመስንቆ ድምፅ እያሰሙ አታሞ ይመቱ ነበር።