ከእኔ የምታገኙት ጥቅም ዘላቂ ሀብትና ዕድገት የእኔ ናቸው። ከንጹሕ ወርቅና ከተነጠረ ብር የሚሻል ነው።
ፍሬዬ ከንጹሕ ወርቅ ይበልጣል፤ ስጦታዬም ከነጠረ ብር።
ፍሬዬም ከምዝምዝ ወርቅ ይሻላል፥ ቡቃያዬም ከተመረጠች ብር።
ከወርቅና ከከበረ ዕንቍ ይልቅ እኔን መምረጥ ይሻላል፥ ፍሬዬም ከጠራ ብር ይሻላል።
ጥበብ በንጹሕ ወርቅ አትገዛም፤ ዋጋዋም በብር አይተመንም።
‘ቶጳዝዮን’ የተባለ የኢትዮጵያ ዕንቊ አይተካከላትም፤ እጅግ በጠራ ወርቅም አትገመትም።
የደግ ሰው ንግግር እንደ ነጠረ ብር ነው፤ የክፉ ሰው አሳብ ግን ዋጋቢስ ነው።
ወርቅን ከማግኘት ጥበብን ማግኘት ይበልጣል፤ ብርንም ከማግኘት ዕውቀትን ማግኘት ይሻላል።
ስለዚህ ጥበብ ከብር ይበልጥ ትርፍ ትሰጣለች፤ ከወርቅም የተሻለ ጥቅም ታስገኛለች።
ከብር ይልቅ ምክሬን ምረጡ፤ ከንጹሕ ወርቅ ይልቅ ዕውቀትን ምረጡ።
የእኔ መንገድ የጽድቅ መንገድ ነው፤ እኔ የምከተለው የፍትሕን ፈለግ ነው።
ጥበብ እንደ ገንዘብ ከለላ ነች፤ ከዚያም በላይ ጥበብ ገንዘብ ላደረጋት ሕይወትን ትጠብቃለች።