እንደ ነጋዴ መርከብ ወደ ሩቅ ስፍራዎች በመሄድ ልዩ ልዩ ዐይነት ምግቦችን ትሰበስባለች።
እንደ ንግድ መርከብ፣ ምግቧን ከሩቅ ትሰበስባለች።
እርሷ እንደ ነጋዴ መርከብ ናት፥ ከሩቅ አገር ምግብዋን ትሰበስባለች።
ከኦፊር ወርቅ ያመጡ የንጉሥ ኪራምና የንጉሥ ሰሎሞን ሰዎች ከዚያው ከኦፊር የሰንደል እንጨትና ዕንቊ ለሰሎሞን አምጥተውለት ነበር፤
ከሱፍ ክርና ከበፍታ ልብስ በመስፋት ደስ እያላት በሥራ ትጠመዳለች።
የበፍታ ልብስ እየሠራች ትሸጣለች፤ ለነጋዴዎችም ድግ ታስረክባለች።
ዘወትር በሥራ ተጠምዳ ቤተሰብዋን ስለምትንከባከብ ስንፍና አይገኝባትም።