የማሳ አገር ሰው የያቄ ልጅ አጉር በጥሞና የተናገራቸው ንግግሮች የሚከተሉት ናቸው፦ “አምላክ ሆይ! ደክሜአለሁ፤ አምላክ ሆይ! ደክሜአለሁ፤ እንዴት ልቋቋመው እችላለሁ?
የያቄ ልጅ የአጉር ቃል ይህ ነው፤ ይህ ሰው ለኢቲኤል፣ ለኢቲኤልና ለኡካል ተናገረ፤
የማሣ አገር ሰው የያቄ ልጅ የአጉር ቃል። ሰውየው ለኢቲኤልና ለኡካል እንደዚህ ይናገራል፦
ክፉ ሰዎች በደጋግ ሰዎች ዘንድ የተጠሉ ናቸው፤ ደጋግ ሰዎችም በክፉ ሰዎች ዘንድ ይጠላሉ።
ከሰውነት ደረጃ ወጥቼ እንደ እንስሳ ሆኛለሁ፤ ሰው ሊኖረው የሚገባው ማስተዋል የለኝም።
ከዚህ የሚከተለው ለማሳው ንጉሥ ለልሙኤል እናቱ የሰጠችው ምክር ነው።