ምሳሌ 10:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሰው ላይ መጠቃቀስ ችግርን ያመጣል፤ በግልጥ የሚነቅፍ ግን ሰላም እንዲገኝ ያደርጋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በተንኰለኛ ዐይን የሚጠቅስ ሐዘን ያስከትላል፤ ለፍላፊ ቂልም ወደ ጥፋት ያመራል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዓይኑ የሚጠቅስ መከራን ያመጣል፥ ደፍሮ የሚገሥጽ ግን ሰላምን ያደርጋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለክፋት በዐይኑ የሚጠቃቀስ ለሰው ኀዘንን ይሰበስባል፥ በግልጽ የሚገሥጽ ግን ሰላምን ያደርጋል። |
ስለዚህ ወደ እናንተ ስመጣ እርሱ እየሰደበንና እያዋረደን ያደረገውን ክፉ ሥራ ሁሉ ለሁሉም እናገራለሁ፤ ይህም ሳይበቃው ቀርቶ፤ እርሱ ራሱ ወንድሞችን አይቀበልም። ሌሎችም እንዳይቀበሉአቸው ይከለክላል። ከቤተ ክርስቲያንም ያስወጣቸዋል።