ዐሥራ ሁለቱ ከወርቅ የተሠሩት የዕጣን ማስቀመጫዎች በመቅደሱ ሚዛን መሠረት እያንዳንዳቸው ዐሥር ሰቅል የሚመዝኑ ሲሆኑ በጠቅላላው አንድ መቶ ኻያ ሰቅል ይመዝኑ ነበር።
ዘኍል 7:87 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለሚቃጠል መሥዋዕት የቀረበው የከብት ብዛት ዐሥራ ሁለት ኰርማዎች፥ ዐሥራ ሁለት አውራ በጎች፥ ባለ አንድ ዓመት ዕድሜ የሆኑ ዐሥራ ሁለት ተባት በጎች ከእህል ቊርባናቸው ጋርና ዐሥራ ሁለት ተባት ፍየሎች ለኃጢአት መሥዋዕት፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለሚቃጠል መሥዋዕት የቀረቡት እንስሳት የእህል ቍርባናቸውን ጨምሮ ድምራቸው፦ ዐሥራ ሁለት ወይፈን፣ ዐሥራ ሁለት አውራ በግ፣ ዐሥራ ሁለት አንድ ዓመት የሆናቸው ተባዕት የበግ ጠቦቶች ሆነ፤ እንዲሁም ለኀጢአት መሥዋዕት የቀረቡ ዐሥራ ሁለት ተባዕት ፍየሎች ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሚቃጠለው መሥዋዕት ከብት ሁሉ ዐሥራ ሁለት ወይፈኖች፥ ዐሥራ ሁለትም አውራ በጎች፥ ዐሥራ ሁለትም የአንድ ዓመት ተባት ጠቦቶች ከእህሉ ቁርባን ጋር ነበሩ፤ የኃጢአትም መሥዋዕት አውራ ፍየሎች ዐሥራ ሁለት ነበሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሚቃጠለው መሥዋዕት ከብት ሁሉ ከእህሉ ቍርባን ጋር ዐሥራ ሁለት ወይፈኖች፥ ዐሥራ ሁለትም አውራ በጎች፥ ዐሥራ ሁለትም የአንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦቶች ነበሩ፤ የኀጢአትም መሥዋዕት አውራ ፍየሎች ዐሥራ ሁለት ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሚቃጠለው መሥዋዕት ከብት ሁሉ ከእህሉ ቍርባን ጋር አሥራ ሁለት ወይፈኖች፥ አሥራ ሁለትም አውራ በጎች፥ አሥራ ሁለትም የአንድ ዓመት ተባት ጠቦቶች ነበሩ፤ የኃጢአትም መሥዋዕት አውራ ፍየሎች አሥራ ሁለት ነበሩ። |
ዐሥራ ሁለቱ ከወርቅ የተሠሩት የዕጣን ማስቀመጫዎች በመቅደሱ ሚዛን መሠረት እያንዳንዳቸው ዐሥር ሰቅል የሚመዝኑ ሲሆኑ በጠቅላላው አንድ መቶ ኻያ ሰቅል ይመዝኑ ነበር።
ለአንድነት መሥዋዕት የቀረቡት የከብት ብዛት፦ ኻያ አራት ኰርማዎች፥ ሥልሳ አውራ በጎች፥ ሥልሳ ተባት ፍየሎች፥ ባለ አንድ ዓመት ዕድሜ ሥልሳ ተባት በጎች፥ መሠዊያው ከተቀባ በኋላ ለመቅደስ የቀረበ ቊርባን ይህ ነው።