ዘኍል 7:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፦ “በዐሥራ ሁለት ተከታታይ ቀኖች ውስጥ በእያንዳንዱ ቀን ከዐሥራ ሁለቱ አለቆች አንዱ መሠዊያው ለሚቀደስበት ክብረ በዓል የሚሆን መባ ያቀርቡ ዘንድ ንገራቸው።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርም ሙሴን፣ “የመሠዊያውን መቀደስ ምክንያት በማድረግ እያንዳንዱ አለቃ ስጦታውን በቀን በቀኑ ያቅርብ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “አለቆቹ መሠዊያውን ለመቀደስ በእያንዳንዱ ቀን አንድ አለቃ መባውን ያቅርብ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ሙሴን፥ “እያንዳንዱ አለቃ በየቀኑ መሠዊያውን ለመቀደስ እያንዳንዱ አለቃ መባውን በቀን በቀኑ ያቅርብ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ሙሴን፦ አለቆቹ መሠዊያውን ለመቀደስ መባቸውን እያንዳንዱ በቀን በቀኑ ያቅርቡ አለው። |
በሥጋ ከእናንተ ብርቅም እንኳ በመንፈስ ከእናንተ ጋር ነኝ፤ በመልካም ሥነ ሥርዓት መኖራችሁንና በክርስቶስ ላይ ያላችሁን ጽኑ እምነት በማየትም ደስ ይለኛል።