በመጨረሻም በዳን ነገድ ቡድን ሰንደቅ ዓላማ ሥር የሚገኙትና ለሁሉም ክፍሎች ደጀን የሚሆኑት በዓሚሻዳይ ልጅ በአሒዔዜር መሪነት የቡድን ተራቸውን ጠብቀው ተጓዙ።
ዘኍል 2:31 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንደየክፍላቸው በዳን ሰፈር እንዲሰፍሩ የተደረጉት ሰዎች ብዛት አንድ መቶ ኀምሳ ሰባት ሺህ ስድስት መቶ ነበር። በዚህ ዐይነት የዳን ክፍል የመጨረሻ ተራ ተጓዥ ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በየሰራዊታቸው ሆነው ከዳን ምድብ የተመዘገቡት ወንዶች ሁሉ አንድ መቶ ዐምሳ ሰባት ሺሕ ስድስት መቶ ናቸው፤ እነርሱም በዐርማቸው ሥር በመጨረሻ ይመጣሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዳን ሰፈር የተቈጠሩ ሁሉ መቶ ኀምሳ ሰባት ሺህ ስድስት መቶ ነበሩ። እነርሱም በየዓላሞቻቸው በመጨረሻ ይጓዛሉ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዳን ሰፈር የተቈጠሩ ሁሉ መቶ አምሳ ሰባት ሺህ ስድስት መቶ ነበሩ። እነርሱም በየዓላማቸው በመጨረሻ ይጓዛሉ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዳን ሰፈር የተቈጠሩ ሁሉ መቶ አምሳ ሰባት ሺህ ስድስት መቶ ነበሩ። እነርሱም በየዓላሞቻቸው በመጨረሻ ይጓዛሉ። |
በመጨረሻም በዳን ነገድ ቡድን ሰንደቅ ዓላማ ሥር የሚገኙትና ለሁሉም ክፍሎች ደጀን የሚሆኑት በዓሚሻዳይ ልጅ በአሒዔዜር መሪነት የቡድን ተራቸውን ጠብቀው ተጓዙ።
እንደየክፍላቸው በሮቤል ሰፈር እንዲሰፍሩ የተደረጉት ሰዎች ብዛት አንድ መቶ ኀምሳ አንድ ሺህ አራት መቶ ኀምሳ ነበር። በዚህ ዐይነት የሮቤል ክፍል ሁለተኛ ተራ ተጓዥ ይሆናል።
እንደየክፍላቸው በኤፍሬም ሰፈር እንዲሰፍሩ የተደረጉት ሰዎች ብዛት አንድ መቶ ስምንት ሺህ አንድ መቶ ነበር። በዚህ ዐይነት የኤፍሬም ክፍል ሦስተኛ ተራ ተጓዥ ይሆናል።
እንደየክፍላቸው በይሁዳ ሰፈር እንዲሰፍሩ የተደረጉት ሰዎች ብዛት መቶ ሰማኒያ ስድስት ሺህ አራት መቶ ነበር። በመጀመሪያ የሚጓዘው ይህ ቡድን ነበር።