ዘኍል 15:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወይም ምናልባት ወደፊት ዘሮቻችሁ በሙሴ አማካይነት ያዘዘውን ትእዛዝ ሁሉ ሳይፈጽሙ ቢቀሩ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ትእዛዞቹን ከሰጠበት ዕለት ጀምሮ በተከታታይ ትውልዶች በሙሴ አማካይነት ያዘዛችሁን እነዚህን ትእዛዞች ሁሉ ባታደርጉ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ ትዕዛዝን ከሰጠበት ቀን ጀምሮ ወደፊትም እስከ ልጅ ልጃችሁ ጌታ በሙሴ አንደበት ያዘዛችሁን ሁሉ ባታደርጉ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር ካዘዘበት ከፊተኛው ቀን ጀምሮ ወደ ፊትም እስከ ልጅ ልጃችሁ እግዚአብሔር በሙሴ እጅ እንደ አዘዛችሁ ባታደርጉ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር ካዘዘበት ከፊተኛው ቀን ጀምሮ ወደ ፊትም እስከ ልጅ ልጃችሁ እግዚአብሔር በሙሴ እጅ ያዘዛችሁን ሁሉ ባታደርጉ፥ |
እንዲህ ዐይነቱ ስሕተት የተፈጸመው በማኅበሩ አለማወቅ ከሆነ አንድ ወይፈን አምጥተው መዓዛው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ የሚቃጠል መሥዋዕት አድርገው ያቅርቡት፤ ከእርሱም ጋር ተገቢውን የእህልና የወይን ጠጅ ቊርባን ያቅርቡ፤ በተጨማሪም አንድ ተባዕት ፍየል ስለ ኃጢአት ስርየት መሥዋዕት አድርገው ያቅርቡ።