“ለአሮንና ለልጆቹ ለመላውም የእስራኤል ሕዝብ እንዲህ በላቸው፦ እስራኤላዊ የሆነ ወይም በእስራኤላውያን መካከል የሚኖር መጻተኛ ስእለት ተፈጽሞለት ወይም የበጎ ፈቃድ ስጦታ አድርጎ የሚቃጠል መሥዋዕት ቢያቀርብ፥
ዘኍል 15:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእናንተ ጋር ያለ ወይም በመካከላችሁ የሚኖር መጻተኛ መዓዛው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ የምግብ ቊርባን ለእግዚአብሔር ለማቅረብ ቢፈልግ፥ ይህንኑ የሥርዓት መመሪያ በተመሳሳይ ሁኔታ መከተል ይኖርበታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለሚቀጥሉት ትውልዶች ሁሉ መጻተኛ ወይም በመካከላችሁ የሚኖር ማንኛውም ሰው በእሳት የሚቀርብ ሽታው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ መሥዋዕት በሚያቀርብበት ጊዜ ልክ እናንተ እንደምታደርጉት ያድርግ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መጻተኛም ከእናንተ ጋር ቢቀመጥ፥ ወይም በትውልዳችሁ መካከል ማንም ሰው ቢኖር፥ ለጌታ መዓዛው ያማረ ሽታ እንዲሆን በእሳት የሚቀርበውን ቁርባን ቢያቀርብ፥ እናንተ እንደምታደርጉት እርሱ እንዲሁ ያደርጋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መጻተኛም ከእናንተ ጋር ቢቀመጥ፥ ወይም በትውልዳችሁ መካከል ማንም ሰው ቢኖር፥ ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ እንዲሆን ቍርባን በእሳት ቢያቀርብ እናንተ የምታደርጉትን እርሱ እንዲሁ ያደርጋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መጻተኛም ከእናንተ ጋር ቢቀመጥ፥ ወይም በትውልዳችሁ መካከል ማንም ሰው ቢኖር፥ ለእግዚአብሔር ጣፋጭ ሽታ እንዲሆን ቍርባን በእሳት ቢያቀርብ፥ እናንተ የምታደርጉትን እርሱ እንዲሁ ያደርጋል። |
“ለአሮንና ለልጆቹ ለመላውም የእስራኤል ሕዝብ እንዲህ በላቸው፦ እስራኤላዊ የሆነ ወይም በእስራኤላውያን መካከል የሚኖር መጻተኛ ስእለት ተፈጽሞለት ወይም የበጎ ፈቃድ ስጦታ አድርጎ የሚቃጠል መሥዋዕት ቢያቀርብ፥
“ከባዕድ ሰው የተገኘውን እንስሳ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አድርገህ አታቅርብ፤ እነዚህን የመሳሰሉ እንስሶች ነውር እንዳለባቸው ስለሚቈጠሩ ተቀባይነት የላቸውም።”
የአገር ተወላጅ የሆነ እያንዳንዱ እስራኤላዊ መዓዛው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ የእህል ቊርባን በሚያቀርብበት ጊዜ ይህን ሁሉ ማድረግ ይኖርበታል፤
እናንተም ሆናችሁ በመካከላችሁ የሚኖሩ መጻተኞች ለሚመጡት ዘመናት ሁሉ እነዚህን የሥርዓት መመሪያዎች በተመሳሳይ ሁኔታ መጠበቅ ይኖርባችኋል፤ እናንተም ሆናችሁ እነርሱ በእግዚአብሔር ፊት አንድ ናችሁ።