ዘኍል 15:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም ግማሽ ሊትር የወይን ጠጅ የመጠጥ ቊርባን አድርገህ ታቀርባለህ፤ ይህም ለእግዚአብሔር መልካም መዓዛ የሚሆን የሚቃጠል መሥዋዕት ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲሁም ለመጠጥ ቍርባን የሚሆን ግማሽ ሂን የወይን ጠጅ አቅርቡ፤ ይህም በእሳት የሚቀርብና ሽታው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ መሥዋዕት ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለጌታም መዓዛው ያማረ ሽታ እንዲሆን በእሳት የሚቀርብ ቁርባን አድርገህ፥ የኢን መስፈሪያ ግማሽ የወይን ጠጅ ለመጠጥ ቁርባን ታቀርባለህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ እንዲሆን በእሳት ለተደረገ ቍርባን፥ የኢን መስፈሪያ ግማሽ ወይን ለመጠጥ ቍርባን ታቀርባለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለእግዚአብሔር ጣፋጭ ሽታ እንዲሆን በእሳት ለተደረገ ቍርባን፥ የኢን መስፈሪያ ግማሽ የወይን ጠጅ ለመጠጥ ቍርባን ታቀርባለ። |
ደግሞም እርሾ ሳይነካው የተጋገረ አንድ መሶብ እንጀራ፥ በወይራ ዘይት ከተለወሰ ዱቄት የተጋገረ ውፍረት ያለው ኅብስት፥ በወይራ ዘይት የተቀቡ ስስ ቂጣዎች ጭምር ከሚቀርበው ከእህል ቊርባንና ከመጠጥ መባ ጋር አብሮ ይቅረብ።
ጡት ካስጣለችውም በኋላ ወደ ሴሎ ይዛው ወጣች፤ ከእርሱም ጋር የሦስት ዓመት ኰርማ ዐሥር ኪሎ ዱቄትና አንድ አቁማዳ ሙሉ የወይን ጠጅ ይዛ ሄደች፤ ሳሙኤልንም ገና በልጅነቱ በሴሎ ወደሚገኘው ወደ እግዚአብሔር ቤት ወሰደችው፤