ዝናው በሶርያ አገር ሁሉ ስለ ተሰማ፥ ሰዎች በልዩ ልዩ በሽታና ደዌ የሚሠቃዩትን፥ ርኩሳን መናፍስት ያደሩባቸውን፥ የሚጥል በሽታ ያለባቸውንና ሽባዎችንም ሁሉ ወደ እርሱ አመጡ፤ እርሱም ፈወሳቸው።
ማቴዎስ 8:31 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አጋንንቱም “የምታስወጣን ከሆነ፥ እባክህ ወደዚያ ወደ ዐሣማዎቹ መንጋ ስደደን!” ሲሉ ለመኑት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አጋንንቱም ኢየሱስን፣ “የምታስወጣን ከሆነ ዐሣማዎቹ መንጋ ውስጥ እንድንገባ ፍቀድልን” ብለው ለመኑት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አጋንንቱም “የምታስወጣን ከሆነ፥ ወደ ዓሣማው መንጋ ስደደን፤” ብለው ለመኑት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አጋንንቱም “ታወጣንስ እንደሆንህ፥ ወደ እሪያው መንጋ ስደደን፤” ብለው ለመኑት። “ሂዱ፤” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አጋንንቱም፦ ታወጣንስ እንደሆንህ፥ ወደ እሪያው መንጋ ስደደን ብለው ለመኑት። ሂዱ አላቸው። |
ዝናው በሶርያ አገር ሁሉ ስለ ተሰማ፥ ሰዎች በልዩ ልዩ በሽታና ደዌ የሚሠቃዩትን፥ ርኩሳን መናፍስት ያደሩባቸውን፥ የሚጥል በሽታ ያለባቸውንና ሽባዎችንም ሁሉ ወደ እርሱ አመጡ፤ እርሱም ፈወሳቸው።
የተቀደሰውን ነገር ለውሾች አትስጡ፤ ዕንቋችሁንም በዐሣማዎች ፊት አትጣሉ፤ ዐሣማዎቹ ዕንቋችሁን በእግራቸው ይረግጡታል፤ ውሾቹም ተመልሰው ይነክሱአችኋል።
ኢየሱስም “ሂዱ!” አላቸው። ስለዚህም ከሰዎቹ ወጥተው ወደ ዐሣማዎቹ ሄዱና ገቡባቸው። ዐሣማዎቹም በሙሉ ከገደሉ አፋፍ ላይ እየተንደረደሩ ወርደው በባሕር ውስጥ ሰጥመው ሞቱ።
በታላቅ ድምፅም እየጮኸ፥ “አንተ የልዑል እግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ሆይ! አንተ ከእኔ ጋር ምን ጉዳይ አለህ? በእግዚአብሔር ስም እለምንሃለሁ፤ እባክህ አታሠቃየኝ!” አለው።
ስለዚህ ሰማያትና በውስጣቸው የምትኖሩ ሁሉ ደስ ይበላችሁ! ጥቂት ጊዜ ብቻ እንደ ቀረው ስላወቀ ዲያብሎስ በታላቅ ቊጣ ወደ እናንተ ወርዶአልና ምድርና ባሕር ወዮላችሁ!”