ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦ “ሙሴና ሳሙኤል እንኳ በፊቴ ቆመው ቢማልዱ ለዚህ ሕዝብ ምሕረት አላደርግም፤ ስለዚህ ከፊቴ ወዲያ እንዲሄዱ አድርግ።
ማቴዎስ 25:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ብልኆቹ ልጃገረዶች ግን ‘ለእኛና ለእናንተ የሚበቃ ዘይት የለንም። ይልቅስ ወደ ሱቅ ሂዱና ለእናንተ የሚሆን ዘይት ግዙ’ ሲሉ መለሱላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “አስተዋዮቹ ልጃገረዶች ግን መልሰው፣ ‘ያለን ዘይት ለእኛም ለእናንተም ላይበቃ ስለሚችል፣ ሄዳችሁ ከሻጮች ለራሳችሁ ግዙ’ አሏቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ብልሆቹ ግን ‘ለእኛና ለእናንተ ላይበቃ ይችላል፤ ይልቅስ ወደሚሸጡት ሄዳችሁ ለራሳችሁ ግዙ’ ሲሉ መለሱላቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልባሞቹ ግን መልሰው ‘ምናልባት ለእኛና ለእናንተ ባይበቃስ፤ ይልቅስ ወደሚሸጡት ሄዳችሁ ለራሳችሁ ግዙ፤’ አሉአቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ልባሞቹ ግን መልሰው፦ ምናልባት ለእኛና ለእናንተ ባይበቃስ፤ ይልቅስ ወደሚሸጡት ሄዳችሁ ለራሳችሁ ግዙ አሉአቸው። |
ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦ “ሙሴና ሳሙኤል እንኳ በፊቴ ቆመው ቢማልዱ ለዚህ ሕዝብ ምሕረት አላደርግም፤ ስለዚህ ከፊቴ ወዲያ እንዲሄዱ አድርግ።
ስለዚህ እኔ እግዚአብሔር ሕያው አምላክ እንደ መሆኔ ኖኅ፥ ዳንኤልና ኢዮብ እንኳ በዚያ ቢኖሩ በጽድቃቸው የራሳቸውን ሕይወት ብቻ ያድናሉ እንጂ የገዛ ልጆቻቸውን እንኳ ማዳን አይችሉም”፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።