ይህንንም ለሰባት ቀን በየዕለቱ አድርግ፤ በዚህም ዐይነት መሠዊያው ፍጹም የተቀደሰ ይሆናል፤ የተቀደሰም ስለ ሆነ፥ ሰውም ሆነ ሌላ ነገር እርሱን ቢነካ በቅድስናው ኀይል ቅሥፈት ይደርስበታል።
ማቴዎስ 23:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ ዕውሮች! ከመባውና መባውን ከሚቀድሰው መሠዊያ የቱ ይበልጣል? አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናንተ ዕውሮች፤ ከመባውና መባውን ከቀደሰው መሠዊያ የቱ ይበልጣል? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንተ ዕውሮች! የትኛው ይበልጣል? መባው ወይስ መባውን የሚቀድሰው መሠዊያው? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እናንተ ደንቆሮዎችና ዕውሮች! ማናቸው ይበልጣል? መባው ነውን? ወይስ መባውን የሚቀድሰው መሠዊያው? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናንተ ደንቆሮዎችና ዕውሮች፥ ማናቸው ይበልጣል? መባው ነውን? ወይስ መባውን የሚቀድሰው መሠዊያው? |
ይህንንም ለሰባት ቀን በየዕለቱ አድርግ፤ በዚህም ዐይነት መሠዊያው ፍጹም የተቀደሰ ይሆናል፤ የተቀደሰም ስለ ሆነ፥ ሰውም ሆነ ሌላ ነገር እርሱን ቢነካ በቅድስናው ኀይል ቅሥፈት ይደርስበታል።
በዚህ ዐይነት እነዚህን ሁሉ በመለየት ፍጹም የተቀደሱ ታደርጋቸዋለህ፤ እነርሱንም ፍጹም ቅዱሳን ስለ ሆኑ ሰውም ሆነ ሌላ ነገር ቢነካቸው ቅሥፈት ይደርስበታል።
ለምሳሌ አንድ ሰው የተቀደሰ ሥጋ ከመሠዊያ ላይ ወስዶ በመጐናጸፊያው ጠቅልሎ ቢይዝ፥ ልብሱም እንጀራና ወጥ፥ የወይን ጠጅና ዘይት ወይም ማናቸውንም ዐይነት ምግብ ቢነካ፥ ምግቡ ሁሉ በዚያ ሰው ምክንያት የተቀደሰ ሊሆን ይችላልን?” በላቸው፤ በዚህ መሠረት ነቢዩ ከጠየቃቸው በኋላ፥ ካህናቱ “የተቀደሰ ሊሆን አይችልም” ሲሉ መለሱ።