የባቢሎን ንጉሥ በመስቀለኛ መንገዶቹ መታጠፊያ አጠገብ ይቆማል፤ በየትኛው መንገድ መሄድ እንዳለበት ለማወቅ ፍላጻዎችን ይወረውራል፤ ጣዖቶቹንም ምክር ይጠይቃል፤ ለመሥዋዕት ከታረደ እንስሳ የጒበት ሞራ ወስዶም ይመረምራል።
ማቴዎስ 22:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ በየአውራ ጐዳናው ሂዱና ያገኛችሁትን ሰው ሁሉ ወደ ሠርጉ ግብዣ ጥሩ።’ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወደ መንገድ መተላለፊያ ወጥታችሁ ያገኛችሁትን ሁሉ ወደ ሰርጉ ድግስ ጥሩ።’ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ወደ መንገድ መተላለፊያ ሄዳችሁ ያገኛችሁትን ሁሉ ወደ ሰርጉ ጥሩ።’ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንግዲህ ወደ መንገድ መተላለፊያ ሄዳችሁ ያገኛችሁትን ሁሉ ወደ ሰርጉ ጥሩ፤’ አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንግዲህ ወደ መንገድ መተላለፊያ ሄዳችሁ ያገኛችሁትን ሁሉ ወደ ሰርጉ ጥሩ አለ። |
የባቢሎን ንጉሥ በመስቀለኛ መንገዶቹ መታጠፊያ አጠገብ ይቆማል፤ በየትኛው መንገድ መሄድ እንዳለበት ለማወቅ ፍላጻዎችን ይወረውራል፤ ጣዖቶቹንም ምክር ይጠይቃል፤ ለመሥዋዕት ከታረደ እንስሳ የጒበት ሞራ ወስዶም ይመረምራል።
የሚሸሹትን ለመግደል በመስቀልኛ መንገድ ላይ ባላደባህባቸውም ነበር፤ የተረፉትንም በመከራቸው ቀን ለጠላት አሳልፈህ መስጠት ባልተገባህም ነበር።”
እኔ ከቅዱሳን ሁሉ የማንስ ብሆንም እንኳ ወሰን የሌለውን የክርስቶስን ባለጸግነት ለአሕዛብ እንዳበሥር በእግዚአብሔር ጸጋ ይህ ዕድል ተሰጠኝ።
መንፈስ ቅዱስና ሙሽራይቱ “ና!” ይላሉ፤ የሚሰማም “ና!” ይበል፤ የተጠማም ይምጣ፤ የፈለገም የሕይወትን ውሃ ያለ ምንም ዋጋ በነጻ ይጠጣ።