ማቴዎስ 21:45 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያን እነዚህን ምሳሌዎች በሰሙ ጊዜ ኢየሱስ የተናገረው ስለ እነርሱ መሆኑን ተገነዘቡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያን ምሳሌዎቹን በሰሙ ጊዜ፣ ስለ እነርሱ የሚናገር መሆኑን ዐወቁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሊቃነ ካህናትና ፈሪሳውያን ምሳሌዎቹን በሰሙ ጊዜ ስለ እነርሱ እንደ ተናገረ አወቁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያንም ምሳሌዎቹን ሰምተው ስለ እነርሱ እንደ ተናገረ አስተዋሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያንም ምሳሌዎቹን ሰምተው ስለ እነርሱ እንደ ተናገረ አስተዋሉ፤ |
የሕግ መምህራንና የካህናት አለቆች ይህን ምሳሌ በእነርሱ ላይ እንደ ተናገረ ዐውቀው በዚያን ሰዓት ሊይዙት ፈልገው ነበር፤ ነገር ግን ሕዝቡን ፈሩ።