ማቴዎስ 20:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ይሄድ ነበር፤ በመንገድም ሳሉ ዐሥራ ሁለቱን ደቀ መዛሙርት ለብቻቸው ወደ እርሱ ወስዶ እንዲህ አላቸው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም በመሄድ ላይ ሳለ ዐሥራ ሁለቱን ደቀ መዛሙርት ለብቻቸው ወስዶ እንዲህ አላቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ሲወጣ ሳለ፥ ዐሥራ ሁለቱን ደቀ መዛሙርት ለብቻቸው ወሰዳቸው፥ በመንገድም ሳሉ እንዲህ አላቸው፦ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ሊወጣ ሳለ፥ በመንገድ ዐሥራ ሁለቱን ደቀ መዛሙርት ብቻቸውን ወደ እርሱ አቅርቦ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ሊወጣ ሳለ፥ በመንገድ አሥራ ሁለቱን ደቀ መዛሙርት ብቻቸውን ወደ እርሱ አቅርቦ፦ |
አገልጋይ ጌታው የሚያደርገውን ስለማያውቅ ከእንግዲህ ወዲህ አገልጋዮች አልላችሁም፤ ነገር ግን ከአባቴ የሰማሁትን ሁሉ ስለ ገለጥኩላችሁ ወዳጆቼ ብያችኋለሁ፤
የተገለጠውም አስቀድሞ በእግዚአብሔር ለተመረጡት ምስክሮች ነው እንጂ ለሕዝቡ ሁሉ አይደለም፤ እርሱ ከሞት ከተነሣ በኋላ እኛ ከእርሱ ጋር አብረን የበላንና የጠጣን ምስክሮቹ ነን፤