ማቴዎስ 18:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ መንግሥተ ሰማይ ከአገልጋዮቹ ጋር ሊተሳሰብ የፈለገውን ንጉሥ ትመስላለች፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ስለዚህ መንግሥተ ሰማይ፣ በባሪያዎቹ እጅ የነበረውን ሒሳብ ለመተሳሰብ የፈለገን ንጉሥ ትመስላለች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ስለዚህ መንግሥተ ሰማያት ከባርያዎቹ ጋር ሊተሳሰብ የፈለገን ንጉሥ ትመስላለች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ስለዚህ መንግሥተ ሰማያት ባሮቹን ሊቈጣጠር የወደደን ንጉሥ ትመስላለች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ መንግሥተ ሰማያት ባሮቹን ሊቍኦጣጠር የወደደን ንጉሥ ትመስላለች። |
ደግሞም ኢየሱስ ይህን ምሳሌ ነገራቸው፦ “መንግሥተ ሰማይ አንዲት ሴት ወስዳ ከሦስት መስፈሪያ ዱቄት ጋር የለወሰችውን እርሾ ትመስላለች፤ እርሾውም ሊጡን ሁሉ እንዲቦካ አደረገው።”
ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “እንዲሁም መንግሥተ ሰማይ ወደ ባሕር የተጣለች መረብን ትመስላለች፤ እርስዋ በየዐይነቱ ዓሣ የምትሰበስብ ናት፤
እርሱም “እንግዲያውስ የመንግሥተ ሰማይን ምሥጢር ጠንቅቆ የሚያውቅ የሕግ መምህር፦ ከዕቃ ግምጃ ቤቱ አዲስ የሆነውንና አሮጌ የሆነውን ዕቃ የሚያመጣ የንብረት ባለቤትን ይመስላል” ሲል መለሰላቸው።
ኢየሱስም እንዲህ ሲል ሌላ ምሳሌ ነገራቸው፦ “በዚያን ጊዜ ወደ መንግሥተ ሰማይ የመግባት ሁኔታ እንዲህ ይሆናል፦ አንድ ወደ ሌላ አገር የሚሄድ ሰው አገልጋዮቹን ጠርቶ ንብረቱን እንዳስረከባቸው ዐይነት ይሆናል።
ስለዚህ ጊዜው ሳይደርስ፥ ጌታ ለፍርድ ከመምጣቱ በፊት በማንም ላይ አትፍረዱ፤ እርሱ በሚመጣበት ጊዜ በጨለማ የተሰወረውን ምሥጢር ወደ ብርሃን ያወጣዋል፤ በሰዎች ልብ የተደበቀውን ሐሳብ ይገልጠዋል፤ በዚያን ጊዜ እያንዳንዱ ከእግዚአብሔር ተገቢውን ምስጋና ያገኛል።