ማቴዎስ 15:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “እናንተስ ወጋችሁን ለመጠበቅ ብላችሁ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ስለምን ታፈርሳላችሁ? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፤ “እናንተስ ለወጋችሁ ስትሉ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ለምን ትሽራላችሁ? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም “እናንተስ ስለ ልማዳችሁ ስትሉ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ለምን ትተላለፋላችሁ? ሲል መለሰላቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም መልሶ እንዲህ አላቸው “እናንተስ ስለ ወጋችሁ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ስለ ምን ትተላለፋላችሁ? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ እናንተስ ስለ ወጋችሁ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ስለ ምን ትተላለፋላችሁ? |
እነዚህ ትእዛዞች ከገዛ ፈቃድ በመነጨ አምልኮና በአጉል ትሕትና፥ ሰውነትንም በማጐሳቈል ላይ ስለሚያተኲሩ ጥበብ ያላቸው ይመስሉ ይሆናል፤ ነገር ግን ሥጋዊ ስሜትን በመቈጣጠር ረገድ ዋጋቢሶች ናቸው።
በክርስቶስ ላይ የተመሠረተ ሳይሆን በሰው ሠራሽ ወግና በዓለማዊ ተራ ሥርዓት ላይ በተመሠረተ በፍልስፍናና በከንቱ ሽንገላ ማንም እንዳያጠምዳችሁ ተጠንቀቁ።