ማቴዎስ 14:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደቀ መዛሙርቱም “እኛ እዚህ ያለን አምስት እንጀራና ሁለት ዓሣ ብቻ ነው” አሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም፣ “በዚህ ያለን ዐምስት እንጀራና ሁለት ዓሣ ብቻ ነው” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱም “ከአምስት እንጀራና ከሁለት ዓሣ በቀር በዚህ ምንም የለንም” አሉት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱም “ከአምስት እንጀራና ከሁለት ዓሣ በቀር በዚህ የለንም፤” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱም፦ ከአምስት እንጀራና ከሁለት ዓሣ በቀር በዚህ የለንም አሉት። |
ገና የማታስተውሉ ናችሁን? አምስት እንጀራ ለአምስት ሺህ ሰው እንደበቃና የተረፈውን ፍርፋሪ ምን ያኽል መሶብ ሙሉ እንዳነሣችሁ አታስታውሱምን?
ኢየሱስ ግን “እናንተ ራሳችሁ የሚበሉትን ስጡአቸው፤” አላቸው። እነርሱም “እኛ ያለን አምስት እንጀራና ሁለት ዓሣ ብቻ ነው፤ ስለዚህ ሄደን ምግብ ካልገዛን በቀር ለዚህ ሁሉ ሕዝብ አይበቃም፤” አሉት።