ለብሼው የነበረውንም ልብስ በማውለቅ አራግፌ “ከእናንተ መካከል ማንም ሰው የገባውን የተስፋ ቃል ቢያፈርስ እግዚአብሔር እንደዚህ ያድርገው፤ ቤት ንብረቱንም ወስዶ ባዶ እጁን ያስቀረው” አልኳቸው። በዚያም የተገኘው ሰው ሁሉ በአንድ ድምፅ “አሜን!” በማለት እግዚአብሔርን አመሰገነ፤ መሪዎቹም የገቡትን ቃል ፈጸሙ።
ማቴዎስ 10:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ማንም ሰው የማይቀበላችሁ ወይም ቃላችሁን የማይሰማ ቢሆን ያንን ቤት ወይም ከተማ ለቃችሁ ስትወጡ የእግራችሁን ትቢያ አራግፉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ማንም ሰው ሊያስተናግዳችሁ ወይም የምትናገሩትን ሊሰማ ፈቃደኛ ካልሆነ፣ ከቤቱ ወይም ከከተማው ስትወጡ የእግሮቻችሁን ትቢያ አራግፋችሁ ውጡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ማንም የማይቀበላችሁ ወይም ቃላችሁን የማይሰማ ከሆነ ከዚያ ቤት ወይም ከዚያች ከተማ የእግራችሁን ትቢያ አራግፉችሁ ውጡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከማይቀበላችሁም ቃላችሁንም ከማይሰሙ ሁሉ፥ ከዚያ ቤት ወይም ከዚያች ከተማ ስትወጡ የእግራችሁን ትቢያ አራግፉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከማይቀበላችሁም ቃላችሁንም ከማይሰሙ ሁሉ፥ ከዚያ ቤት ወይም ከዚያች ከተማ ስትወጡ የእግራችሁን ትቢያ አራግፉ። |
ለብሼው የነበረውንም ልብስ በማውለቅ አራግፌ “ከእናንተ መካከል ማንም ሰው የገባውን የተስፋ ቃል ቢያፈርስ እግዚአብሔር እንደዚህ ያድርገው፤ ቤት ንብረቱንም ወስዶ ባዶ እጁን ያስቀረው” አልኳቸው። በዚያም የተገኘው ሰው ሁሉ በአንድ ድምፅ “አሜን!” በማለት እግዚአብሔርን አመሰገነ፤ መሪዎቹም የገቡትን ቃል ፈጸሙ።
ሰዎች በማይቀበሉአችሁና በማይሰሙአችሁ ቦታ ሁሉ የእግራችሁን አቧራ አራግፉና ከዚያ ወጥታችሁ ሂዱ፤ ይህም ለእነርሱ የማስጠንቀቂያ ምስክር ይሆንባቸዋል።”
እርሱም “ይህን ሕፃን በስሜ የሚቀበል ሁሉ እኔን ይቀበላል፤ እኔንም የሚቀበል ሁሉ የላከኝን ይቀበላል። ከእናንተ መካከል ከሁላችሁም የሚያንስ እርሱ ከሁሉ የሚበልጥ ይሆናል፤” አላቸው።
ነገር ግን አይሁድ በተቃወሙትና በሰደቡት ጊዜ የልብሱን ትቢያ አራግፎ “እንግዲህ ቢፈረድባችሁ በራሳችሁ ጥፋት ነው! እኔ ኀላፊነት የለብኝም፤ ከእንግዲህ ወዲህ ወደ አሕዛብ እሄዳለሁ!” አላቸው።