ከዚህ በኋላ ሎጥ ሴቶች ልጆቹን ወዳጩአቸው ሰዎች ቤት ሄደና “ቶሎ ብላችሁ ከዚህ ውጡ፤ እግዚአብሔር ይህን ስፍራ ሊደመስሰው ነው” አላቸው፤ እነርሱ ግን የሚቀልድ መስሎአቸው ቸል አሉ።
ማርቆስ 5:40 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰዎቹም በማፌዝ ሳቁበት፤ ኢየሱስ ግን ሁሉንም ከቤት አስወጣ፤ የልጅትዋን አባትና እናት ከእርሱም ጋር የነበሩትን አስከትሎ፦ ልጅትዋ ወደነበረችበት ክፍል ገባ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰዎቹ ግን ሣቁበት። ሰዎቹን ሁሉ ከቤት ካስወጣ በኋላ፣ የብላቴናዪቱን አባትና እናት እንዲሁም ዐብረውት የመጡትን ደቀ መዛሙርት አስከትሎ ብላቴናዪቱ ወዳለችበት ገባ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰዎቹም ሳቁበት። እርሱ ግን ሁሉን አስወጣ፤ የልጅቱንም አባትና እናት እንዲሁም አብረውት የመጡትን አስከትሎ ልጅቱ ወዳለችበት ገባ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በጣምም ሳቁበት። እርሱ ግን ሁሉን አስወጥቶ የብላቴናይቱን አባትና እናት ከእርሱ ጋር የነበሩትንም ይዞ ብላቴናይቱ ወዳለችበት ገባ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በጣምም ሳቁበት። እርሱ ግን ሁሉን አስወጥቶ የብላቴናይቱን አባትና እናትም ከእርሱ ጋር የነበሩትንም ይዞ ብላቴናይቱ ወዳለችበት ገባ። |
ከዚህ በኋላ ሎጥ ሴቶች ልጆቹን ወዳጩአቸው ሰዎች ቤት ሄደና “ቶሎ ብላችሁ ከዚህ ውጡ፤ እግዚአብሔር ይህን ስፍራ ሊደመስሰው ነው” አላቸው፤ እነርሱ ግን የሚቀልድ መስሎአቸው ቸል አሉ።
ነገር ግን ሰንባላጥና ጦቢያ እንዲሁም ጌሼም ተብሎ የሚጠራው አንድ የዐረብ ተወላጅ እኛ ያወጣነውን የሥራ ዕቅድ በሰሙ ጊዜ በእኛ ላይ እየዘበቱ በመሳቅ “ይህ የምትሠሩት ሥራ ምንድን ነው? ወይስ በንጉሠ ነገሥቱ ላይ ማመፅ ትፈልጋላችሁን?” ሲሉ ጠየቁን።
እግዚአብሔርን ጠርቼው የመለሰልኝ ጊዜ ነበር፤ አሁን እኔ የወዳጆቼ መሳቂያ ሆኛለሁ፤ ስሕተት የሌለብኝ ፍጹሙ እኔ የሰው ሁሉ መሳለቂያ ሆኛለሁ።
የተቀደሰውን ነገር ለውሾች አትስጡ፤ ዕንቋችሁንም በዐሣማዎች ፊት አትጣሉ፤ ዐሣማዎቹ ዕንቋችሁን በእግራቸው ይረግጡታል፤ ውሾቹም ተመልሰው ይነክሱአችኋል።