እንዲሁ እነርሱ በመቃብሮች መካከል የሚቀመጡ፥ በድብቅ ቦታዎች ሌሊቱን የሚያሳልፉ፥ የእሪያ ሥጋ የሚበሉ፥ በዕቃቸውም ውስጥ የረከሰ ወጥ የሚያኖሩ ናቸው።
ማርቆስ 5:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህ ሰው በመቃብር ቦታ ይኖር ነበር፤ ማንም በሰንሰለት እንኳ አስሮ ሊያቈየው አይችልም ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህ ሰው በመቃብር ቦታ ውስጥ የሚኖርና ማንም በሰንሰለት እንኳ ሊያስረው የማይችል ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህ ሰው በመቃብር ቦታ ውስጥ የሚኖርና ማንም በሰንሰለት እንኳ ሊያስረው የማይችል ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም በመቃብር ይኖር ነበር፤ በሰንሰለትም ስንኳ ማንም ሊያስረው በዚያን ጊዜ አይችልም ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም በመቃብር ይኖር ነበር፥ በሰንሰለትም ስንኳ ማንም ሊያስረው በዚያን ጊዜ አይችልም ነበር፤ |
እንዲሁ እነርሱ በመቃብሮች መካከል የሚቀመጡ፥ በድብቅ ቦታዎች ሌሊቱን የሚያሳልፉ፥ የእሪያ ሥጋ የሚበሉ፥ በዕቃቸውም ውስጥ የረከሰ ወጥ የሚያኖሩ ናቸው።
ብዙ ጊዜ በእግር ብረትና በሰንሰለት ይታሰር ነበር፤ ነገር ግን ሰንሰለቱን እየበጣጠሰና እግር ብረቱንም እየሰባበረ ይጥል ነበር፤ ስለዚህ ይዞ ሊያቆመው የሚችል ማንም አልነበረም።
ይህንንም ያለበት ምክንያት ኢየሱስ ርኩሱን መንፈስ ከሰውየው እንዲወጣ አዞት ስለ ነበር ነው። ከዚህ በፊት ርኩሱ መንፈስ በሰውየው ላይ ብዙ ጊዜ ይነሣበት ነበር፤ በሰንሰለትና በእግር ብረት እየታሰረ ይጠበቅ ነበር፤ ይሁን እንጂ ሰንሰለቱን ይበጥስ፥ እግር ብረቱንም ይሰብር ነበር። ጋኔኑም እየነዳ ወደ በረሓ ይወስደው ነበር።