ቀኑ ሊመሽ ሲል፥ ዐሥራ ሁለቱ ደቀ መዛሙርት ወደ ኢየሱስ ቀርበው፥ “ይህ ያለንበት ቦታ በረሓ ነው፤ ስለዚህ ሰዎቹ በአካባቢው ወዳሉት ከተሞችና ገጠሮች ሄደው ምግብና ማደሪያ እንዲፈልጉ አሰናብታቸው፤” አሉት።
ሉቃስ 9:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስ ግን “እናንተ ራሳችሁ የሚበሉትን ስጡአቸው፤” አላቸው። እነርሱም “እኛ ያለን አምስት እንጀራና ሁለት ዓሣ ብቻ ነው፤ ስለዚህ ሄደን ምግብ ካልገዛን በቀር ለዚህ ሁሉ ሕዝብ አይበቃም፤” አሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱ ግን፣ “የሚበሉትን እናንተው ስጧቸው” አላቸው። እነርሱም፣ “ለዚህ ሁሉ ሕዝብ የሚበቃ ምግብ ሄደን ካልገዛን በቀር፣ እኛ ያለን ከዐምስት እንጀራና ከሁለት ዓሣ አይበልጥም” አሉት፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱ ግን፦ “እናንተ የሚበሉትን ስጡአቸው፤” አላቸው። እነርሱም፦ “ሄደን ለዚህ ሁሉ ሕዝብ ምግብ ካልገዛን በቀር ከአምስት እንጀራና ከሁለት ዓሣ የሚበልጥ የለንም፤” አሉት፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱ ግን፥ “እናንተ የሚበሉትን ስጡአቸው” አላቸው፤ እነርሱም፥ “ለዚህ ሁሉ ሕዝብ የሚበቃ ምግብ ልንገዛ ካልሄድን ከአምስት እንጀራና ከሁለት ዓሣ በቀር ሌላ በዚህ የለንም” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱ ግን፦ እናንተ የሚበሉትን ስጡአቸው አላቸው። እነርሱም፦ ሄደን ለዚህ ሁሉ ሕዝብ ምግብ ካልገዛን፥ ከአምስት እንጀራና ከሁለት ዓሣ የሚበልጥ የለንም አሉት፤ |
ቀኑ ሊመሽ ሲል፥ ዐሥራ ሁለቱ ደቀ መዛሙርት ወደ ኢየሱስ ቀርበው፥ “ይህ ያለንበት ቦታ በረሓ ነው፤ ስለዚህ ሰዎቹ በአካባቢው ወዳሉት ከተሞችና ገጠሮች ሄደው ምግብና ማደሪያ እንዲፈልጉ አሰናብታቸው፤” አሉት።