ከእናንተ መካከል እግዚአብሔርን የሚፈራና ለአገልጋዩ ቃል የሚታዘዝ ማነው? ብርሃን የሌለው በጨለማ የሚመላለስ በእግዚአብሔር ይታመን፤ እምነቱንም በአምላኩ ላይ ይጣል።
ሉቃስ 8:50 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስ ግን ይህን ሰምቶ ኢያኢሮስን፥ “አይዞህ አትፍራ፤ እመን ብቻ፤ ልጅህ ትድናለች፤” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሱስም ይህን ሰምቶ ኢያኢሮስን፣ “አትፍራ፤ እመን ብቻ እንጂ፤ ልጅህ ትድናለች” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢየሱስ ግን ይህን ሰምቶ ለኢያኢሮስ መልሶ እንዲህ አለው፦ “አትፍራ፤ እመን ብቻ፤ እርሷም ትድናለች።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጌታችን ኢየሱስም በሰማ ጊዜ የምኵራቡን ሹም፥ “አትፍራ፥ ብቻ እመን፤ ልጅህስ ትድናለች” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢየሱስ ግን ሰምቶ፦ አትፍራ፤ እመን ብቻ ትድንማለች ብሎ መለሰለት። |
ከእናንተ መካከል እግዚአብሔርን የሚፈራና ለአገልጋዩ ቃል የሚታዘዝ ማነው? ብርሃን የሌለው በጨለማ የሚመላለስ በእግዚአብሔር ይታመን፤ እምነቱንም በአምላኩ ላይ ይጣል።
ኢየሱስ ወደ ኢያኢሮስ ቤት በደረሰ ጊዜ ከጴጥሮስ፥ ከዮሐንስ፥ ከያዕቆብ፥ ከልጅትዋ አባትና እናት በቀር ሌላ ማንም ከእርሱ ጋር ወደ ውስጥ እንዲገባ አልፈቀደም።
ስለ አብርሃም፦ “የብዙ ሕዝብ አባት አድርጌሃለሁ” ተብሎ ተጽፎአል፤ ይህም ተስፋ ለአብርሃም የተሰጠው እርሱ የሞቱትን በሚያስነሣውና የሌለውን እንዲኖር በሚያደርገው አምላክ ስለ አመነ ነበር።